እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:09:47 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:09:47 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ስፖርት
ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊቀነስ ነው
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
አዲሱ የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና በየዓመቱ የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ውድድር ግሪክ እንድታዘጋጅ መመረጧን የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል፡፡
ኢትዮጵያን በዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች ካሳወቋት ውደድሮች አንዱ ማራቶን ነው።
ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ዓለምን ያሰደመመው ይህንን ረጅሙን ሩጫ በማሸነፉ ነበር።
ከአራት ዓመታት በቶኪያ ይህንን 42ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ለሁለተኛ ጊዜ በዓለም ገናና የሆነው በማራቶን አሸንፎ ነው።
አትሌት ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሆና የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው በዚህ ረጅም ርቀት ተወዳድራ አሸንፋ ባገኘችው ውጤት ነው።
ከኃይሌ ገብረ ሥላሴ እስከ ታምራት ቶላ፤ከአሰለፈች መኩሪያ እስከ ቲኪ ገላና ያሉት ኢትዮጵያውያን ማራቶንን ሮጠው ድል አስመዝግበዋል።
የዓለምን አትሌቲክስን ወድድሮች የሚያዘጋጀው አካል ከአራት ዓመታት በኋላ በሚያዘጋጃቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ ማራቶንን እንደማያካትት ያመላከትበት መግለጫ አውጥቷል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2030 ጀምሮ ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ውጪ ይሆናል ብሏል፡፡
ነገር ግን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027ና በ2029 በሚካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎቾ የውድድሩ አካል ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ከዚያ በኋላ ግን ማራቶን የሚስተናገድበት አዲስ ዓመታዊ የአትሌቲክስ ውድድር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡
በዚህም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2030 የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና የሚል ራሱን የቻለ ውድድር ይጀምራል፡፡
አዲሱ የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና በየዓመቱ የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ውድድር ግሪክ እንድታዘጋጅ መመረጧን የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል፡፡
ስፖርት
አትሌቲክስ
ማራቶን
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!