እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ማይክሮ ሶፍት ለዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች የደህንነት ማሻሻያ ለቀቀ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ማሻሻያ ለማግኘት "Settings" ውስጥ በመግባት "Windows Update" የሚለውን መምረጥ፣ ከዚያም "Check for Updates" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን ማውረድና መጫን እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
ማይክሮሶፍት ኩባንያ የዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ኮምፒውተራቸውን ከጥቃት የሚከላከል አዲስ የደህንነት ማሻሻያ ይፋ አድርጓል፡፡
ምንም እንኳን ለዊንዶውስ 10 የሚደረገው መደበኛ ድጋፍ ቢቋረጥም፣ ማይክሮሶፍት ክፍያ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ተቋማት እስከ ጥቅምት 2028 የሚቆይ ነው፡፡
ኩባንያው "Extended Security Update (ESU)" የተሰኘ ልዩ የድጋፍ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
ይህ አሰራር ተቋማት ወደ ዊንዶውስ 11 ለመሸጋገር ተጨማሪ ጊዜ እንዲያገኙ ታሳቢ ያደረገ የሽግግር ጊዜ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል፡፡
ይህ የቀረበዉ አዲስ ዝመና በዋናነት በኮምፒዩተር ላይ የተገኙ 79 የደህንነት ክፍተቶችን ለመድፈን የወጣ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ አስቀድሞ በጠላፊዎች እጅ ገብተው ጥቃት እያደረሱ የነበሩ አደገኛ ስጋቶች ናቸው፡፡
በመሆኑም ይህንን ማሻሻያ መጫን የኮምፒዩተርን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ኩባንያው ገልጿል።
ከደህንነት ጥበቃው ጎን ለጎን፣ ዝመናው በአንዳንድ መሣሪያዎች ላይ ይታይ የነበረውን ያለመጥፋት (Shut down) ችግር ይፈታል ብሏል።
ቀደም ሲል "System Guard Secure Launch" የሚባለው የደህንነት ሲስተም በስራ ላይ በሚሆንበት ወቅት፣ ኮምፒዩተሮች ሙሉ በሙሉ ለመጥፋት ወይም ወደ "Sleep" ሁኔታ ለመግባት ይቸገሩ ነበር፤ አዲሱ ማሻሻያ ግን ይህንን የቴክኒክ ስህተት ሙሉ በሙሉ አስተካክሎታል።
በተጨማሪም በቅርቡ ጊዜያቸው የሚያልፉ የደህንነት ሰርተፊኬቶችን በአዲስ በመተካት፣ ኮምፒዩተሮች ለወደፊት ለጥቃት እንዳይጋለጥ ያደርጋል።
ይህንን ማሻሻያ ለማግኘት "Settings" ውስጥ በመግባት "Windows Update" የሚለውን መምረጥ፣ ከዚያም "Check for Updates" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን ማውረድና መጫን እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
ማሻሻያው በተሳካ ሁኔታ ከተጫነ በኋላ የኮምፒውተሩ የጥበቃ ስሪት ወደ "Build 19045.7058" ከፍ ይላል።
ኩባንያው እንደገለጸው ዝመናው ምንም ዓይነት የታወቀ የቴክኒክ ችግር ስለማያስከትል ተጠቃሚዎች በልበ ሙሉነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዊንዶውስ 10
ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!