እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:02 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች

ሞቀም ቀዘቀዘም ምርጫ 2018 ከፊታችን ነው

5 ደቂቃ ንባብ
ሞቀም ቀዘቀዘም ምርጫ 2018 ከፊታችን ነው

በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ዘንድሮ ትኩረት የተሰጠው ለኮሪደር ልማትና ለመልሶ ግንባታ እንጂ፡ ለምርጫ አይደለም የሚሉ አስተያየቶች ይሰማሉ፡፡ገዢው ፓርቲ ምርጫውን በአሸናፊነት እንደሚወጣ በመተማመኑ ለምርጫው ትኩረት አልሰጠም ሲባል መስማት የተለመደ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡

ምርጫ ከነወዙ ዱሮ ቀረ በማለት  የምርጫ 1997 ማስታወሻቸውን የሚያወጡ ዜጎች አልታጡም፡፡የምርጫ ክርክሮች በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግን በኢንተር አፍሪካ ግሩፕና በተለያ አካላት የተካሄዱበት፣ የከተማ ውስጥ ቅሰቀሳዎች በድምጸ ማጉያዎች፣ በፖስተሮችና አልፎ ተርፎም ቤት ለቤት የተደረገበት ዘመን ያስታወሱ፡፡

የናይጄሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2027 ለሚካሄድ ምርጫ ቅሰቀሳ የጀመሩት ገና 2025  ነው የሚሉም ገጥመዋል፡፡

ኬንያውያን በቀጣይ ዓመት ለሚደረግ ምርጫ ዛሬ ሞቅ ያለ እንቅስቃሴ በመታየት ላይ ነው የሚሉም አላጣንም፡፡

ገዢው ፓርቲ ቢቀሰቅስ ወይም ባይቀሰቅስ የራሱ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ተፎካካሪዎቹ ማን ከለከላቸው ብሎ ነገሩን ገልብጦ ማየት ያስፈልጋል፡፡

በአገሪቴ ምርጫ ከሁለት አሥርት ወዲህ በ2002፣በ2007ና በ2013 ምርጫዎች ተካሂደዋል፡፡ያሸነፈው ፓርቲ መንግሥት ሆኖ አገር አስተዳድሯል፡፡

አዎን ለምርጫ 2018 ዝግጅት እተደረገ ነው፡፡አሁን በምርጫው ዋነኛ ሂደት ላይ እንገኛለን፡፡ከድምፅ መስጫው ዕለት ወዲህ ባለው እንቅስቃሴ፡፡በዚህ ሂደት እስካሁን ለምርጫው 11ሺህ ዕጩዎች  በፖለቲካ ፓርቲዎችና በግል መመዘገባቸው ለመራጭነት ደግሞ ከ42 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተመዝግበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያዎች  ዘመኑን በመጠነ ልክ የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ ጥረት እያደረገ ነው፡፡የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረረጥ፣የምርጫ ቁሳቁስ በማጓጓዝና በመሰል ችግሮች እንዳጋጠሙት አሳውቋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን የዜጎችን የፖለቲካ ንቃተ-ህሊና በማሳደግና የፖለቲካ እሳቤዎቻቸውን በነፃነት እንዲያንሸራሸሩ ምቹ መድረክ በመፍጠር ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምሰሶ ናቸው።በተለይም በምርጫ ወቅት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል የክርክርና የዘገባ ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ሕዝቡ በቂ መረጃ ኖሮት  ድምፅ  እንዲሰጥ ያስተምራሉ።

መገናኛ ብዙኃን ለምርጫ ሂደት ስኬት ገንቢ ሚና የሚወጣ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገንቢያ መሣሪያ መሆኑን ያምናሉ፡፡ መጪው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያ እንደሆን ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና የምርጫ ዘገባዎችን በዜና እና ዜና ነክ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀር በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ተደራሽ እያደረጉ መሆናቸውን  ገልጸዋል፡፡

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የክርክር መድረኮችና ዘገባዎችን በማዘጋጀት ተደራሽ እያደረጉ መሆኑንና በፖለቲካ ፖርቲዎች መካከል በሃሳብ የበላይነት የተመሰረተ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን ለማጎልበት በተለያዩ ቋንቋዎች የንግግር ባህል ለማጎልበት መድረኮች እየፈጠርን ሲሉም ተናግረዋል።

መገናኛ ብዙኃን ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፈጥሯቸው መድረኮች ዜጎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦችን እንዲገነዘቡ ፍትሐዊ የአየር ሰዓት ድልድል በመፍጠር ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጫቸውን በነፃነት ለሕዝብ የሚሸጡበት መድረክ ተመቻችቶ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫም የኢትዮጵያን በሃሳብ የበላይነት የተመሰረተ የፖለቲካ ባህል መገንባት የሚያስችል ምቹ የመገናኛ ብዙኅን ምኅዳር በመፍጠር እየተሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።

መገናኛ ብዙኃን የፈጠሯቸው የፖሊሲ አማራጭ የክርክር መድረኮች ከዚህ ቀደም የነበረውን የመወቃቀስና መካሰስ አካሄድ በመቀየር ተስፋ ሰጪ የዴሞክራሲ ምኅዳር እየተፈጠረ መሆኑን የገለጹት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለሥልጣን ተናግረዋል።

በቀጣይም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፍትሐዊ የአየር ሰዓትና የዘገባ ሽፋን በመስጠት በሐሳብ የበላይነት ለተመሰረተ የፖለቲካ ፉክክር መጎልበት የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን እናጠናክራለን ብለዋል።

ይህነ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ በሕጋዊ መንገድ ተቋቁመው ወደ ምርጫው የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት የሚያደርጉት ተሳትፎ ለምርጫው ከ50 ቀናት በታች በቀሩበት ጊዜ የምርጫ እንቅሰቃሴያቸው ፈዛዛ ነው የሚል አስተያየቶች ግን አሉ፡፡ከ20ዓመታት የነበረውን በማስታወስ ብቻ ሳይሆን፤የዛሬዪቱን ኢትዮጵያንና የምንኖርባትን ዓለም አይመጥኑም የሚሉ፡፡

ፓርቲዎች የምርጫ ፉክክሮች ከመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችና የምርጫ ፉክክሮች ያለፉ ሆነው እምብዛም አልታዩም፡፡የዘንድሮው ምርጫ ‹‹የተቀዛቀዘ›› የሚል ቅጥያ ባያጣም፤የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙኃን በዕለት ተዕለት የዜና ዘገባዎቻቸው ሽፋን ለመስጠት ይሞክራሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አሁን ሁሉም መገናኛ ብዙኃን የአየር ሰዓታቸውንና የጋዜጣ ዓምዶቻቸውን ለምርጫ ቅሰቀሳ ሰጥተዋል፡፡በተለይ እንደ ኢ ቢ ኤስ ያሉ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለአምስት ጥያቄዎች አምስት ደቂቃ በመስጠት የፓርቲዎችን ፖሊሲዎችና አቋሞች እንዲያብራሩ ዕድል የሚሰጡበት ፕሮግራም ፈጥረዋል፡፡

በተለይ የመራጮች አስተያየቶችን ዘሉ ዘገባዎች በየቀኑ መስማት የተለመደ ክስተት ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ 

የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የሚያደርጓቸው የምርጫ ክርክሮች አነሰም አደገም ለምርጫው ሕይወት እየሰጡት ነው፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በተለይም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን(ኢቢሲ)ና ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ኤግንባር ቀደም በመሆን ክርክሮቹን ማስተናገድ ጀምረዋል፡፡ዘግይቶም ቢሆን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ(ኤኤም ኤን)ና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሸን(አሚኮ) ተቀላቅለዋቸዋል፡፡

በአፋን ኦሮሞና በአፋርኛ ቋንቋዎች የምርጫ ክርክሮች መስተናገድ የተጀመረበት ሁኔታም ተፈጥሯል፡፡

የምርጫ ክርክሮቹ በዴሞከራሲ ሥርዓት ፣በፈዴራሊዝም ሥርዓትና በሕገ መንግሥት፣በውጭ ግንኙነትና ብሔራዊ ደህንነትና በሰላም፣በግብርና፣በትምህርት፣ኢኮኖሚ፣ጤና፣ቱሪዝም፣ማዕድንና ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡

እካሁን በተደረጉት ክርክሮች  አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል፡፡ ከነዚህም በሁሉም ማለትም በሁለቱ አገራዊ፣በአዲስ አበባ አስተዳደርና በአማራ ክልል ስያሜ ባላቸው ቴሌቪዥን ስርጭት ባላቸው (ምንም እንኳን በዚህ ዘመን ስርጭቶች ዓለም አቀፍ ቢሆኑም)፡፡ በተጨማሪም በዩቲብና በሌሎች ማሀበራዊ መገናኛ ብዙኃን የሚስተናግዱበት እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡

ክርክሮቹ መራጮች ፓርቲዎቹ ያሏቸውን አማራጮች አውቆ ድምጹን ለሚፈልግ ፓርቲ ለመምረጥ እንደሚረዱት ይታመናል፤ይህም የመራጭነት ካርድ ለማውጣት በማነሳሳትም ድርሻ ነበራቸው፡፡

በአገሪቱ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውን አስተዋውቀውና አባላትን አፍርተዋል፣ደጋፊዎችን አሰባስበዋል፡፡ አሁን ደግሞ ፈረሱም ሜዳውም ነውና አሁን ደግሞ ሕዝብ  በሚሰጣቸው ድምጽ ላይ ተመስርተው አገር የሚመሩበት የመንግሥት ሥልጣን ለማግኘት ለመያዝ ኳሱ በሜዳና በእግራቸው ላይ ናት፡፡ኳሷን በደጋፊዎች ታግዞ ግብ ማስቆጠር  ይጠበቅባቸዋል፡፡ያለዚያ በዝግ ስታዲየም መጫወት ይሆንባቸዋል፡፡ድምጽ ያለችው በአያንዳንዱ ድምጽ ሰጪ እጅ ናትና፡፡

በዘንድሮው የፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙኃን  የምርጫ ክርክሮች አንድ ጥሩ አየታዘብን ነው፡፡በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዕጣ  የደረሷቸውን የመወዳደሪያ ምልክቶች በምርጫው አሸንፈው እንዲወጡ ጥሩ መቀስቀሻ አድርገው ሲጠቀሙባቸው ይታያል፡፡የያዙትን ሲያከብሩና ሲወዱ የሚፈልጉትን ለማግኘት ያግዛል፡፡የፓርቲዎቻቸን ብልህነትና ብልጥነት ያስደሰታል፡፡

ፓርቲዎቻችን በሊበራል፣በለዝብተኛ ሊበራል ማህበራዊ ሊበራልም ይሁን በሌላ ርዕዮተ ዓለም ይመሩ ለኢትዮጵያ ይበጃታልና ያዋጣታል የሚሉት አማራጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ይዘው ዛሬ በመገናኛ ብዙኃን ቀርበዋል፡፡ነገ ወደ ሕዝቡ በአካል ቀርበው የሚቀሰቅሱበት ጊዜ ነው፡፡

የምርጫ ክርከሮች ከመገናኛ ብዙኃን ውጭ የሚገኙና ይህንን ለማከናወን ፈቃድ ያላቸው አካላት የሚካሄድበት ሁኔታ ቢፈጠር፡፡ቦርዱ በራሱ ያደረግ እንደተጠበቀና ሌሎች ከርክሮችን እንደሚያዘጋጅ ተስፋ ይደረጋል፡፡

የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙኃን በተለይም የክልሎቹ ክርክሮችን በየራሰቸው የሥራ ቋንቋዎች በተከታታይ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ክርከሮቹ በቀጣዮቹ ሣምንታት አድማሳቸውን አስፍተው በሌሎች ወሳኝነት ባላቸው የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ አማራጭ የሚሏቸውን ፖሊሲዎች አትኩረው እንዲቀጥሉ ቢደረግ መልካም ይሆናል፡፡

የምርጫ ክርከረሮች በጨዋነትና ሥነ ምግባር በተሞላበት መንገድ ማካሄድ ከመዘላለፍና ከመሰዳደብና መሰል ተግባራት መውጣት፤ ከልክ  ያለፈ የሥነ ምግባር  ጉድለትና ጥሰት ሆነው በሕግ ስለሚያስጠይቁም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ተፎካካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫ ክርከሮች ሲቀርቡ በቂ ዝግጅት አድርገወ መቅረብ አለባቸው፡፡አገርን ባሉኝ አማራጭ ፖሊሲ እመራለሁ የሚል ፓርቲ በደቂቃዎች ተሰፍሮ በተሰጠው ጊዜ ራሱን መሸጥ ሲያቅተው ማየት ያስተዛዝባል ብቻ  ሳይሆን፤ የመራጩን ድምጽ ያሳጣል፡፡

ተፎካካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫ ክርከሮች ሲቀርቡ በቂ ዝግጅት አድርገወ መቅረብ አለባቸው፡፡አገርን ባሉኝ አማራጭ ፖሊሲ እመራለሁ የሚል ፓርቲ በደቂቃዎች ተሰፍሮ በተሰጠው ጊዜ ራሱን መሸጥ ሲያቅተው ማየት የሚያስተዛዝብ ብቻ  ሳይሆን፤ የመራጩን ድምጽ ያሳጣል፡፡

በምርጫ ክርክሮች ተፎካካሪዎችን በአግባቡ መመከት ራስንም ማስከበር ብሎም በሌሎች መከበር ነው፡፡

ክርክሮቹ የሁለንተናዊ መልኳ የተሻለች አንድነቷ የተጠበቀ፣የጋራ መግባባት የሰፈነባት ሰላምና ዴሞከራሲ ሰፈነባትና  የበለፀገች አገር ለመፍጠር የሚረዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ፣ በአፍሪካ አህጉርና በዓለም አቀፍ አደባባዮች ተጠቃሽና ሞዴል አገር ከመፍጠር አኳያ ተቃኝተው እንዲካሄዱ ማድረግ ይጠበቃል፡፡

የሕዝብን ድምጽ በምርጫ አግኝቶ አገር ለመምራት ወደ ግንቦት 24 እየተቃረብን ነው፡፡ ዛሬ‹‹ተቀዛቀዘ›› ያልነው የምርጫ እንቃስቃሴ በሂደት እየሞቀና እየተጋጋለ መሄዱ አይቀርም፡፡ሞቀም ቀዘቀዘም ድምጻችንን ይወክናል ለምንለው ፓርቲ ሰጥተን መንግሥት ሆኖ መምራቱ አይቀርም፡፡ስለዚህ መራጮች ከአሁኑ ምርጫችንን ማስተካከል አለብን፡፡

ድኀረ ግንቦት 24 ደግሞ ሁሉም ነገር ሰክኖ ወደ ትክክለኛው ሁኔታ መመለሱም እሙን ነው፡፡ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫው ጊዜ ሰሌዳ ተጠቅመን ምርጫውን ከቆፈን አናውጣው፡፡ በሰለጠነና ሰላማዊ  በሆነ መንገድ የምርጫ ቅሰቀሳ ሕጋዊ በሆኑ ሥፍራዎችና ባሉት መገናኛ ብዙኃንና ማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን በቀሪው ጊዜ አካሂ,ዱ፡፡ኢትዮጵያ በዚህም ረገድ በአርአያነት የምትጠቀስ አገር እናድርጋት፡፡

 

 


ምርጫ ቦርድምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!