እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:46 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

ሽንብራን በጨረቃ

1 ደቂቃ ንባብ
ሽንብራን በጨረቃ
shinbira 01
1 / 3

ሽንብራ በጨረቃ ላይ የሚበቅል የመጀመሪው ሰብል ሊሆን ነው፡፡

ወደ ጨረቃ የሚደረጉ ጉዞዎች መንኩራኮሮችንና ሰዎችን ብቻ ላይወሰን መሆኑን የአርዝ ዶት ኮም ዘገባ ያመለክታል፡፡

ጠፈርተኞች የተፈጥሮ አፍ በሌለበት ቦታ ለሚኖራቸው ቆይታ ምግብ የሚያመርቱበት አስተማማኝ ሁኔታ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

በቅርቡ የወጣ የምርምር ግኝት እንደሚያመለክተው፤በጨረቃ ላይ ሽንብራ ለማምረት የተጀመረው ጥረት ለስኬት እየተቃረበ ነው፡፡

ለዚህም ሳይንቲስቶች ሽንብራን የጨረቃ በሚመስል አፈር በማብቀልና በማምረት ውጤታማ ሆነዋል፡፡ይህም ሰብሉን ጨረቃ ላይ ለማብቀል ያስችላል የሚል እምነት አሳድሯል፡፡

ይህም ሽንብራን ጨረቃ ላይ ወስዶ ለማልማት ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን አመላካች ነው ብሏል ዘገባው፡፡

ግኝቱ በኀዋ ግብርና ዝርዎችን ከሙከራ ደረጃ አውጥቶ ወደ ምርት ለማስገባትና ምግብ በኀዋ ውስጥ በማምረት ጠፈርተኞች የሚገጥማቸውን የምግብ ችግር ያቃልላል የሚል ተስፋ አሳድሯል፡፡

ሽንብራ ጨረቃ ላይ ለማልማት የተመረጠው በፕሮቲን የበለጸገ፣በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለመመረት የሚችልና ብዙ ውሃ ወይም ማዳበሪያ የማይፈልግ ሰብል በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

 

Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!