እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:04 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

በሕገ ወጥ መንገድ ሊወጣ የነበረ ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ ተያዘ

1 ደቂቃ ንባብ
በሕገ ወጥ መንገድ ሊወጣ የነበረ ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ ተያዘ

በሕገ ወጥ መንገድ ከከተማዋ ሊወጣ የነበረ ስድስት በርሜል ነዳጅ ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ ሲሆን፣የድርጊቱ ፈጻሚዎችበማደያው በነዳጅ መቅዳት ሙያ ላይ በየተሰማራ ግለሰብና አሽከርካሪ ናቸው። 

ግለሰቦቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ከተጠቀሰው የነዳጅ ማደያ የቀዱትን ስድስት በርሜል ወይም 1ሺህ 200 ሊትር ነዳጅ ኮድ 3 A 55857 አዲስ አበባ የሆነ ተሽከርካሪ ሲያዘዋውሩ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5  በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

 ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ባደረገው ምርመራም ነዳጁን በሕገ ወጥ መንገድ ከከተማዋ ለማስወጣት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ገልጿል። 

ወቅታዊውን የዓለም ነዳጅ ቀውስ  እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ነዳጅ  በሕገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ፣ ነዳጅ የሚደብቁና መሰል የወንጀል ድርጊቶች ውስጥ በሚሳተፉ ነዳጅ ማደያዎች፣ ሠራተኞችና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ሕጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ መምሪያው አስጠንቅቋል።

ወንጀልሕገ ወጥ ድርጊትፖሊስ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!