እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:05 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:05 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሕግና ፍትሕ
በነዳጅ ስርጭትና ግብይት የሚታዩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ቁጥጥር ተጠናክሯል
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
በሕገ-ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ 250ሺህ221 ሊትር ቤንዚን እና 198ሺህ 432 ሊትር ናፍጣ ተይዞ ተወርሷል።
1 / 3
አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት በሂደት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ተሰፋፍቷል።
ኢራን ወደ እሥራኤልና የአሜሪካ አጋር ናቸው ወደምትላቸው አገሮች ጭምር ሚሳዬሎችን ድሮኖች በመተኮስ ጥቃት ከምታደርስባቸው መካከል የነዳጅ ምንጮች የሆኑ ጉድጓዶች፣ማከማቻዎችና ማጣሪያዎች ይገኙባቸዋል።
በተመሳሳይም ጥምር ኃይሉ የኢራን የነዳጅ ሀብት የሚያጠፋና የሚያወድሙ እርምጃዎች መውሰዱ አልቀረም።
ከዚህም አልፎ ኢራን የዓለም 20 በመቶ የንግድ መተላለፊያ መሥመር የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ(ወሽመጥ)በመዝጋቷ ሸቀጦችን ነዳጅ የጫኑ መርከቦች መንቀሳቀስ አልቻሉም።
እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ተደማምረው ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ አገሮች ችግር ውስጥ ወድቀዋል።በተለይ የአስያና የአፍሪካ አገሮች።
ከዚህም የተነሳ አገሮች በእጃቸው ያለውን ነዳጅ ለመቆጠብ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ መገደበ፣ከቤት መሥራትን መፍቀድና የሥራ ቀናትን መቀነስን የመሰሉ እርምጃዎች እየወሰዱ መሆናቸውን ዘገባዎች ያሳያሉ።
በኢትዮጵያም በዚህ ሣምንት መግቢያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነዳጅ በቁጠባ ጥቅም ላይ እንዲውል አሳስበዋል።
ማሳሰቢያውን ተከትሎሞ የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ነዳጅ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የተወሰኑ ዘርፎች እንዲሰጥ አዟል።
በተጨማሪሞ መመሪያውን አክብረው በማይሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቆ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ወደ ትግበራ ተገብቷል።
በነዳጅ ስርጭትና ግብይት ሂደት ላይ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር በስድስት ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተጀመረው የተቀናጀ ዘመቻ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
ባለፉት ቀናትም በተደረገው ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።
በዚህም በድርጊቲ ተሳትፈው የተገኙ 613 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ከንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሕገ-ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ 250ሺህ221 ሊትር ቤንዚን እና 198ሺህ 432 ሊትር ናፍጣ ተይዞ ተወርሷል።
ከተወረሰው ነዳጅ መካከል በሽያጭ እንዲውል የተደረገው 48ነጥብ 6ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ ሆኗል።
በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች፣ የሬጉላቶሪ ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶችና ሠራተኞች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ አካላት ይገኙበታል።
ይህም እርምጃው በታችኛው መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በውሳኔ ሰጪዎች ላይም ያነጣጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
በተቀናጀ መልኩ የሚካሄደው ቁጥጥርበዘርፉ የሚታየውን ችግር ለማቃለልና ፍትሃዊ የነዳጅ ስርጭት እንዲኖር እንቅስቃሴው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ብለዋል ሚኒስትሩ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የገጠመውን የነዳጅ ገበያ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ነዳጅ አከፋፋዮችና መላው ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ነዳጅን በቁጠባና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የተጀመረው የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣ በሕገ-ወጥ ተግባር ላይ በሚሰማሩ አካላት ላይም መንግሥት የማይለወጥ አቋም እንደያዘ ተመልክቷል።
ወንጀል
ሕገ ወጥ ድርጊት
ሕገ ወጥ ነዳጅ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!