እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:38 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

በኢትዮጵያ ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ

1 ደቂቃ ንባብ
በኢትዮጵያ ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ
logo of Ethiopian National Election Board
አዲስ አበባ የካቲት 28 ቀን 2018 

ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደገለጸው፤ ለአንድ ወር የሚዘልቅ የመራጮችን ምዝገባ በዲጂታልና በማኑዋል ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመራጮችን ምዝገባ በዲጂታል ለማከናወን ''ምርጫዬ'' የተሰኘ የሞባይል መተግበሪ ሥራ ላይ አንደዋለ ገልጾ፤ዜጎች መተግበሪያወን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር በማውረድ በራሳችው መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

በአገሪቱ ከሶሰት ሺህ በላይ የኢንተርኔት ተደራሸነት ባለባቸወ አካባቢዎች ምዝገባውን ለማከናወን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ትናንት ገልጸዋል፡፡

በምርጫ ጣቢዎች በአካል ቀርበው ለሚመዘገቡ ዜጎች ታብሌት ኮምፒተሮችን ለምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰራጨቱንም አስታውቀዋል፡፡

በግንቦት ወር በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር 10ሺህ 934 ዕጩዎች በ47 ፓርቲዎችና በግል መቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ከነዚህም 73ቱ በግል ቀረቡ ናቸው፡፡

ከዕቹዎቹ 2ሺሀ 198ቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎቸ ይወዳደራሉ፤8ሺሀ 736ቱ ደግሞ በክልል ምክር ቤቶች ወንበር ለማግኘት ይፎካከራሉ፡፡

 

 

 


ETHIOPIA

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!