እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:07 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ በማዕድን ለሚያለሙ ሦስት ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰ

1 ደቂቃ ንባብ
በኢትዮጵያ በማዕድን ለሚያለሙ ሦስት ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰ
በኢትዮጵያ ልማት ዘርፍ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የማዕድን ሲደረግ የዛሬው ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡
1 / 2

ማዕድን ሚኒስቴር በፖታሽ፣ በብረትና በወርቅ ማዕድን ምርት ለሚሰማሩ ሦስት ኩባንያዎች ዛሬ ፈቃድ ሰጠ፡፡

ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሲገቡ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ወጪ እንደሚደረግባቸው  ስምምነቱ በተፈረመበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ልማት ዘርፍ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ስምምነት ሲደረግ የዛሬውን የመጀመሪያውና ታሪካዊ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በፖታሽ ምርት፣ ለዜድ ዋይቲ ቢ ዲ አይ ኤም በብረት ምርት እንዲሰማራ ፈቃዱ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እንዲሁም በወርቅ ምርት እንዲሰራ ቤሮ ማይኒንግ ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ኩባንያዎቹ በሁለት ዓመታት ውስጥም ወደ ምርት እንደሚገቡም በዚሁ ወቅት ተገልጧል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (/ኢትዮጵያ  በማዕድን ዘርፍ ያላትን ሀብት በተገቢው መንገድ ለማልማት ወሳኝ ርምጃዎችን እየወሰደች መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ለኩባንያዎቹ የተሰጠው ፈቃድ ማዕድናቱን ወጥነት ባለው መልኩ ለማምረትና ለውጭ ገበያ በማቅረብ አገሪቱን ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ስትራቴጂያዊ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት የምርት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አቅም ይፈጥራል ሲሉም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ምርቶቹን ከውጭ ለማስገባት  ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት  አስተዋፅኦ እንደሚኖረው  ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

ማዕድን የኢትዮጵያ ብዝኃ ዘርፍ ከተዋቀረባቸው አምስት ምሰሶዎች አንዱ ነው፡፡ዘርፉ በተያዝወ በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሰባት ወራት 3ነጥብ 14 ቢሊዮን ዶላር በማስገኘት ቀዳሚ ሆኗል፡፡

ዘርዱን ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ግብርና በተጠቀሰው ጊዝ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ያስገኘው ገቢ  2ነጥብ 22 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

 

 

 

ስምምነትማዕድን

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!