እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:46:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ባንኩ ለካሪቢያን አገሮች የሚያቀርበውን ፋይናንስ አምስት ቢሊዮን ዶላር አሳደገ

1 ደቂቃ ንባብ
ባንኩ ለካሪቢያን አገሮች የሚያቀርበውን ፋይናንስ አምስት ቢሊዮን ዶላር አሳደገ
የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም) ለካሪቢያን አገሮች የሚያቀርበውን ፋይናንስ ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር አሳደገ፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኢሎምቢ (ዶ/ር) በካሪቢያን ማህበረሰብ (ካሪኮም) የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት፥ ባንኩ ከካሪቢያን ማህበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነት እያሳደገ ነው፡፡

ባንኩ ለቀጣናው አገሮች የሚያቀርበውን የገንዘብ ድጋፍ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር ማሳደጉን አስታውቀዋል፡፡

 በሚቀጥሉት ሦስትና አራት ዓመታት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ በአግሮፕሮሰሲንግና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ የኢኮኖሚ መዋቅሩን ለማሻሻል እንደሚሰራም ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአገሮቹንን የገቢ ሥርዓት ማዘመንና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ባንኩ ለካሪቢያን ማህበረሰብ የሚደረገው የፋይናንስ ድጋፍ መጨመር ወሳኝ እርምጃ ነው ማለታቸውን ባንኩ  የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡

አገሮቹ የአቅም ግንባታና የንግድ ልውውጥን ለመደገፍ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎችን እንዲያጠናክሩ ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል፡፡

አፍሪኤግዚም ባንክ በአፍሪካና በካሪቢያን አገሮች የሚንቀሳቀስ መቀመጫውን ክፍል ያደረገ ባንክ ነው፡፡



Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!