እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:03 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

ባንኩ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማትን አገደ

1 ደቂቃ ንባብ
ባንኩ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማትን አገደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 26 ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማትን አገደ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 26 ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማትን አገደ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ውስጥ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጣቸው የሥልጣን ወሰን ውጭ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት ሲሰጡ ተገኝተዋል ባላቸው 26 ድርጅቶች ላይ ጥብቅ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

ባንኩ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣አዱሊስ መኒ ትራንስፈር፣ አማል ኤክፕረስ፣ጁባ ኤክፕረስና ዋይስ ትሬዲንግ ያሉ ተቋማትን ጨምሮ በአጠቃላይ 26 ወኪሎች ላይ ክትትልና ግምገማ በማድረግ በዝርዝር ለይቷቸዋል።

ይህን ተከትሎ ሕዝቡ ከእነዚህ ተቋማት ጋር ምንም ዓይነት የገንዘብ ዝውውር ግንኙነት እንዳያደርግ አስገንዝቧል።

እነዚህን የታገዱ ወኪሎችም ሆነ ሌሎች የ"ሃዋላ" መረቦችን መጠቀም የኢትዮጵያን ሕግ መጣስ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፣ ተጠቃሚዎች ለከፋ ሕጋዊ ተጠያቂነትና ለገንዘብ መጥፋት አደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ አሳስቧል።

ድርጅቶቹ በሕግ የማይመሩ በመሆናቸው ለሚደርስ የገንዘብ ብክነት ምንም ዓይነት ዋስትና እንደማይኖርም ባንኩ አመላክቷል።
ሕግና ፍትሕወንጀልሕገ ወጥ ገንዘብ አስተላላፊዎቾ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!