እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:46:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ባንኩ ዓመታዊ ጉባዔውን በግብፅ ያካሂዳል

1 ደቂቃ ንባብ
ባንኩ ዓመታዊ ጉባዔውን በግብፅ ያካሂዳል
የፖለቲካና የንግድ ማህበረሰቡን የሚያገናኘው ጉባዔ ዕድገቱ የተጓተተውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ በሚያድግበትና ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስተሳሰር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይወያያል።

የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት(አፍሪኤግዚም)ባንክ 33ኛ ዓመታዊ ጉባዔውን በግብፅ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ባንኩ ባሰራጨው መግለጫ እንዳመለከተው ዓመታዊ ጉባዔውን በሰኔ ወር  አጋማሽ በኒው አላማይን ከተማ ያደርጋል።

የፖለቲካና የንግድ ማህበረሰቡን የሚያገናኘው ጉባዔ ዕድገቱ የተጓተተውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ በሚያድግበትና ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን ትስስር በሚያጠናክሩ መንገዶች ላይ ይወያያል ተብሎም ይጠበቃል።

በጉባዔው የአገሮችና የመንግሥታት መሪዎች፣የማዕከላዊ ባንኮች ገዢዎች፣ኢንቨስተሮችና የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፉበታል።

ተሳታፊዎቹ የአፍሪካ ከፖሊሲ አውጪነት ባሻገር፤በንግድና በምርት  ያስመዘገቡትን ውጤት እንደሚገመግሙም መግለጫው ያስረዳል።

የአፍሪካ እርስ በርስ ንግድን ባጓተቱ ችግሮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ይህም የሎጀስቲክስ እጥረት፣የፋይናንስ እንቅስቃሴ ገደቦችና ደካማ የኢንዱስትሪ አቅምን እንደሚያካትት አመልክቷል።

የማኑፋክቸሪንግን አቅም ማሳደግ፣የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማጠናከርና ከአህጉሪቱ ውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ ሌሎቹ የጉባዔው የትኩረት ነጥቦች መሆናቸውንም ገልጿል።

ጉባዔው የአህጉሪቱ የጋራ ገበያ ለማቋቋም የተጀመረውነ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠናን ለማስፋፋት ጥረቱ በጎለበት ሁኔታ እንደሚካሄድ ያመለከተው መግለጫው፤ባንኩ የሂደቱን እንቅስቃሴ በማጠናከር በቀጣይ ትግበራው በንግድ ተቋማትና በጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ድንበር ተሻጋሪ ሆኖ እንዲሰራበት አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ይሰራል ብሏል።

ከጉባዔው በተጓዳኝ ኩባንያዎችና ባለሀብቶችን የሚያሳትፉ የቢዝነስ መድረኮችና የንግድ ስምምነቶች እንደሚደረሱ የሚጠበቅ ሲሆን፣በነዚህም የንግድ ፍሰትን የሚያፋጥኑና ልውውጦችን የሚያሳድጉ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ልማትን ለማሳደግ ያስችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባንኩ በአህጉሪቱ በሚያደርገው ድጋፍ የንግድ እንቅስቃሴን በማሳደግ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ፣ባለፉት ዓመታት ባደረገው ጥረት ፖሊሲ አውጪዎችን ከኢንዱስትሪ መሪዎች ጋር በማገናኘት የአፍሪካን ንግድ የሚመራባቸውን አቅጣጫዎች ከአገር አልፎ በአህጉር ደረጃ ለመፍጠር አስችያለሁ ብሏል። 





ፋይናንስኢኮኖሚዓመታዊ ጉባዔ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!