እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:46:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ብርቅነሽ የቅድሚያ ለሴቶች ውድድርን በድጋሚ አሸነፈች

1 ደቂቃ ንባብ
ብርቅነሽ የቅድሚያ ለሴቶች ውድድርን በድጋሚ አሸነፈች
አትሌት ብርቅነሽ ደሴ የ23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ አሸንፋለች፡፡
1 / 2

አትሌት ብርቅነሽ ደሴ 23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አሸንፋለች።

ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ  ለ23ኛ ጊዜ "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሀሳብ  ዛሬ ተደርጓል።

በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶችና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ተሳትፈዋል።

በአትሌቶች መካከል  በተደረገው ውድድር ብርቅነሽ ውድድሩን ያሸነፈችው ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ ነው፡፡

የጸደይ ባንክ ስፖርት ክለብን ወክላ የምትወዳደረው ብርቅነሽ አምና ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

መነሻውን መድረሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል በማድረግ በተካሄደው ውድድር ሮቤ ዲዳ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡

ብርቅነሽና ሮቤን   ተከትላ  ሦስተኛ  የወጣችወ ሰናይት ጌታቸው ናት።

ውድድሩን ከ35 ደቂቃ በላይ ተሳታፊዎች በአትሌት መሠረት ደፋር የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡

አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ውድድርም ተካሂዷል፡፡

በሁነቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስጀመሩት ሲሆን፣የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሠረት ደፋር፣ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ውድድሩ የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት 1996 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ስፖርትአትሌቲክስየቅድሚያ ለሴቶች ውድድር

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!