እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:50 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ቦርዱ ምርጫ የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያየ

1 ደቂቃ ንባብ
 ቦርዱ ምርጫ የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተወያየ
ፓርቲዎቹ በለዩዋቸውና ለቦርዱ ባሳወቋቸው አካባቢዎች ላይ በቀጣይ የክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ ያሰማራል።
1 / 2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚደረግባቸው አካባቢዎችን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ።

 የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉን ጨምሮ አምስቱም የቦርድ ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በተደረገው ውይይት ላይ ቦርዱ ቀደም ሲል ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሰበሰበው ሥጋት አለባቸው ብለው የለዩዋቸው አካባቢዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ከተነሡ ተጨማሪ አጀንዳዎች ውስጥም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ያለ የፀጥታ ሥጋትና በነፃነት የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ ሁኔታ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ያለ ምንም ተፅዕኖ ሥራቸውን ማከናወን፣ የፖለቲካ ምኅዳርን በተመለከተ የተቸገሩ መሆናቸው ይጠቀሳሉ። 

ሰብሳቢዋ ቦርዱ በራሱ የደረሰባቸውንና የእርምት ዕርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ያላቸው ጉዳዩችን የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

 ፓርቲዎቹ በለዩዋቸውና ለቦርዱ ባሳወቋቸው አካባቢዎች ላይ በቀጣይ የክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ እንደሚያሠማራ ተናግረዋል።

 ይኽም ከቦርዱ የምርጫ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተውጣጡ ተሣታፊዎች እንደሚኖሩት በማመላከት።

ቦርዱ ቀደም ሲል የክልል ርዕሳነ መስተዳድርና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር  ከንቲባዎች፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ተቋማት አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ማወያየቱን አስታውሷል።

 ቦርዱ በዚሁ ወቅት ከክልሎቹና ከፀጥታ ተቋማት የሰበሰበውን በአረንጓዴ፣ በቢጫና በቀይ የተፈረጀ የፀጥታ ሁኔታ መረጃ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ሰባተኛውን አገራዊ ምርጫ ግንቦት 24ቀን 2018 ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች ነው።

ከዝግጅቱም የፖለቲካ ድርጅቶችንና የግል ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት ዕጩዎች ምዝገባ ተጠናቋል።

ከየካቲት 28ቀን 2018ጀምሮ ደግሞ በመላው አገሪቱ የመራጮች ምዝገባ በመካሄድ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።

ምርጫ ቦርድፓርቲዎችየፖለቲካ ፓርቲዎችምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!