እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:20 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ያስፈልጋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ article

1 ደቂቃ ንባብ
ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ያስፈልጋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ article
በመካከለኛው ምሥራቅ እየተከሰተ ያለው ቀውስ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ በማሳደሩ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ይገባል።

ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ቀውስ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አንዳስገነዘቡት፤ነዳጅን በከፍተኛ ቁጠባና ለመሠረታዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይገባል።

የነዳጅ አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ ሕዝቡ ነዳጅን በከፍተኛ ቁጠባና ለመሠረታዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት አንዲጠቀም አሳስበዋል። 

በተለይም የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎችና የዳጅ ተጠቃሚዎች በኃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ ጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ ይህን ዓለም አቀፋዊ ፈተና በጋራ ለመወጣት የነዳጅ አጠቃቀም ሥርዓታችንን ማስተካከልና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፎች መለየት ይገባል በማለትም አሳስበዋል ።

"ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ አገሮች አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል"ብለዋል።

አሜሪካና እሥራኤል በቅንጅት ኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት የአብዛኛዎቹ የመካለኛው ምሥራቅ አገሮች ሰላምና ፀጥታ ተናግቷል።

ይህንን ተከትሎ ኢራን የዓለም 20 በመቶ ንግድ የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥ በመዝጋቷ የዓለም ንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ገጥሞታል። በዚህም ነዳጅና ሌሎች ሸቀጦች መተላለፊያ አጥተዋል።

በዚህም ሳቢያ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድነዳጅ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!