እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:55 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ባህልና ኪነ-ጥበባት

አገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

1 ደቂቃ ንባብ
አገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ 23ኛው አገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

"የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ የሚደረገው ዝግጅት ለአንድ ሣምንት የሚቆይ ነው።

በዝግጅቱ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ስፖርተኞች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በባህልና ስፖርት ማኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ በአገሪቱ ከ293 በላይ የተመዘገቡ ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች  መኖራቸውን በጥናት  መረጋገጡን ገልጸዋል።

ሆኖም የጨዋታ ሕግና ሥርዓት ተዘርግቶላቸው ውድድር የሚካሄድባቸው ጥቂቶቹ  ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም በጥናት ያልተለዩትን ጨምሮ የባህል ስፖርቶችን ለማወቅና ለማስፋፋት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

መንግሥት የባህል ስፖርትን ቀጣናዊ ትስስርን ለማምጣት፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የየአፍሪካ የባህል ስፖርት ፌስቲቫልን የማስተናገድ ዕድል ማግኘቷን የገለጸት ሚኒስትር ዴኤታው፣ይህንንም ለአፍሪካውያን ለማስተዋወቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሕይወት መሐመድ ዝግጅቱ የባህል ስፖርት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በዘላቂነት በማጠናከር ሚና እንደሚጫወት አስታውቀዋል።

ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ የባህል ስፖርትቶች ውድድሩና ፌስቲቫሉ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚያጠናከርና የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እሴቶችና አብሮነትን ያጎለብታል ብለዋል።








ስፖርትየባህል ስፖርቶች

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!