እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:44 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

ኢትዮ ቴሌኮም ለታዳሽ ኃይል ልማት ትኩረት ሰጥቷል

2 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮ ቴሌኮም ለታዳሽ ኃይል ልማት ትኩረት ሰጥቷል
ኩባንያው አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀ ማድረጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት ትኩረት ሰጥታ በመሥራት ላይ መሆኗ ይታወቃል።

በአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያስመዘገበችው ውጤትም አበረታች ነው።

 ከዚህ በተጓዳኝ ለታዳሽ ኃይል ልማት የሰጠችው ትኩረት የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በአገር ውስጥ ለማዳረስ ከሚደረገው ጥረት ባለፈ፤ለጎረቤትና ለአካባቢው አገሮችም ለመትረፍ አስችሏል።

በአገሪቱ ከታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ እያስመዘገበች ባለው ውጤት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት በማስገባት በቀዳሚነት ከሚጠሩ አገሮች መሆኗ ሲዘገብ ቆይቷል።

ባይሆን ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግሉ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ያለመኖርና ያሉትም በቂ ያለመሆን ዋነኛው ተደርጐ ሲነሳ ቆይቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዘርፍ በወሰደው ተነሳሽነት በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች በማቋቋም አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው።

ጣቢያዎቹ በተለይ በዚህ ዓለም ከፍተኛ ነዳጅ ቀውሰ በገጠማት ወቅት ያላቸው ጠቀሜታ ወደር የሌለው ሆኖ መገኘቱን ሳንዘነጋ።

በተለይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት በመስጠት ነዋሪዎችን እያገለገሉ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በአዳማ ከተማ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል ገንብቶ ዛሬ አገልግሎት አስጀምሯል።

ማዕከሉ በአንድ ጊዜ 12 ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የሚያደርግ አቅም አለው።

አገልግሎቱን ከአዳማ ባሻገር በአካባቢው ከተሞችም ለማስፋት መታቀዱን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ የዲጂታልና የታዳሽ ኃይል ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንና በከተማዋ የተገነባው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከልም የዚሁ ልማት ጥረት አካል ነው ብለዋል።

ጣቢያው እጅግ ፈጣን፤ ኃይል ቆጣቢ፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰራ በመሆኑ፣ ባትሪዎች በሚችሉት ፍጥነት ዘላቂነት ባረጋገጠ መልክ ኃይል እንደሚሞላ ገልጸዋል

አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች  ቻርጀ ማድረጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኩባንያው ቀደም ሲል በአንድ ጊዜ 48 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድጨ የሚችሉ ጣቢያዎችን ወደ ሥራ አሰገብቷል።

ከየካቲት 2017 ጀምሮ ከ284 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ 7ነጥብ 1ኪሎዋት ኃይል መሙላት እንደቻለ አመልክተዋል፡፡

ይህም ከ10ሚሊዮን ኪሎ ግ ራም ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ ይህም ከ49,559 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር ይነጻጸራ ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አብራርተዋል።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ለከተማዋ ስማርት ፕሮጀክት ተቀርፆ አሰራርና አገልግሎትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። 

በከተማዋ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል  ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን በማመላከት።


ኢትዮ ቴሌኮምታዳሽ ኃይልየኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!