እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:44 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

ኢትዮጵያ ከ87 በላይ የጥበቃ ቦታዎች ባለቤት ሆናለች

1 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያ ከ87 በላይ የጥበቃ ቦታዎች ባለቤት ሆናለች
ባለሥልጣኑ ‹‹60 ዓመታት ለኢትዮጵያ የዱር ሕይወት›› በሚል መሪ ሐሳብ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።
1 / 4

ኢትዮጵያ ባለፉት 60 ዓመታት ባደረገችው እንቅስቃሴ 87 በላይ የጥበቃ ቦታዎች ባለቤት መሆኗን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

ባለሥልጣኑ ‹‹60 ዓመታት ለኢትዮጵያ የዱር ሕይወት›› በሚል መሪ ሐሳብ በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ በወቅቱ እንዳሉት፤ ተቋሙ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት በተፈጥሮ ጥበቃ መስክ ስኬት አስመዝግቧል፡፡

የዱር ሕይወት ጥበቃ ላይ የተሳተፉ ሬንጀሮችና የየአካባቢዎቹ ማህበረሰብ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብርቅዬ እንስሳት የብሔራዊ ማንነታችን አካል ናቸው  በማለት ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ብዝኃነት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች ሲሉም አክለዋል።

ሕገ ወጥ አደን፣ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ፣ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥናፋይናንስ  ቀውስ ለዘርፉ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡

ተግዳሮቶችን መፍታት የአንድ ጊዜ ሥራ ብቻ ሳይሆን፤ ሂደት የሚፈልግ መሆኑን አመላክተው፣ለዚህም ሁሉም ባለድርሻዎች በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ  የበርካታ ብርቅና ድንቅ የዱር እንስሳት ባለቤት ስትሆን፤በርካታ ብሔራዊ ፓርኮች እንዳሏት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣንየዱር እንስሳት

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!