እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:31 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:31 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር አገኘች
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ሚኒስቴሩ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሴክተር አፈጻጸም ግምገማን “ተወዳዳሪ ንግድ ሥርዓትና የተሳለጠ የገበያ ትስስር ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር!” በሚል መሪ ቃል ከሚኒስቴሩና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር እያካሄደ ነው።
ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 7ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገለጹ ፡፡
ሚኒስቴሩ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሴክተር አፈጻጸም ግምገማን “ተወዳዳሪ ንግድ ሥርዓትና የተሳለጠ የገበያ ትስስር ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር!” በሚል መሪ ቃል ከሚኒስቴሩና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር እያካሄደ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት
በንግድ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።
በዘርፉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገበው ውጤት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የላቀ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በተለይም በወጪ ንግድ ዘርፍ 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ዕቅዱን 121 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ 2ነጥብ 9 ሚሊዮን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት የዕቅዱን 109 በመቶ እንደተሳካ አስረድተዋል፡፡
ውጤቱ የዘርፉን አዳጊነት የሚያሳይና የድህረ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ሥራዎች የጥፋት ደረጃዎች እየቀነሱ መምጣታቸውን ያሳያል ብለዋል።
የግብይት መሠረተ ልማትን በማስፋፋት የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ቁጥር 2 ሺህ190 መድረሱን እና በኢ-ኮሜርስ ዘርፍም ተጨባጭ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማድረግ ወደ ውጭ ተልከው ይመረመሩ የነበሩ ምርቶች፣ አሁን በእገር ውስጥ ላቦራቶሪዎች እንዲመረመሩ በማድረግ ስኬት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላትን በማበራከትና በማጠናከር ረገድ ውጤት መገኘቱንና በርካታ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ሥራ መግባታቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማኒስቴር
ወጪ ንግድ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!