እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:22 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ5ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች

1 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ5ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች
Meeting 01
1 / 6
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች ከ5 ነጥብ 9ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አገሪቱ አስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ከዘርፉ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እየሰራች መሆኑንም ትናንት የሚኒስቴሩ ባለሥልጣናት ከላኪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተመላክቷል፡፡

አገሪቱ በተጠቀሰው ጊዜ ከዘርፉ ለማስገባት ያቀደው አምስት ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ 

ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከዕቅዱ 117 በመቶ፣ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር ደግሞ 65 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ ተገኝቷል፡፡

ከገቢው ማዕድን 148 በመቶ፣ግብርና 93 በመቶ እንዲሁም ማኑፋክቸሪንግ 86ነጥብ 1 በመቶ አፈጻጸም ማስመዘገባቸው ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለዕቅዱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያደረጉት የምርትና ምርታማነት ማደግ፣መዳረሻ ገበያዎች መሰፋፋት፣በሕገ ወጥ ንግድ ክምችት ላይ ክትትልና ቁጥጥር መጠናከሩና የዓለም ገበያን የተከተለ የዋጋ ክለሳ መደረጉ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ሥርዓቱን የሚያቀላጥፉ ዘመናዊ አሰራሮች መዘርጋታቸውና የገበያ መሠረተ ልማት መስፋፋት አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጸዋል፡፡

በዘርፉ ለተያዝ በጀት ዓመት የተያዘውን ግብ ለማሳካት በቀሪዎቹ ወራት በተቀናጀ መንገድ እንዲሰራ በባለሥልጣናቱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

በተለይም ላኪዎች ምርቶችን  ወደ ገበያ በብዛትና ጥራታቸውን ጠብቀው በማቅረብ አገራዊ ጥቅምን ባስቀደመ መልኩ እንዲሰሩ መጠየቃቸውን መረጃው ያሳያል፡፡

Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!