እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:20 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:20 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ አገኘች
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ50 በመቶ ብልጫ እንደተመዘገበበትም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስምንት ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበቻቸው ምርቶች ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)አስታወቁ።
ከ2ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች መሰጠቱንም ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት አገሪቱ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያቀደችው 5ነጥብ 83 ቢሊዮን ዶላር ነበር።
ሆኖም ከዕቅዱ በ900ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ገቢ ማስገባት ተችሏል ብለዋል።
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ50 በመቶ ብልጫ እንደተመዘገበበትም አስረድተዋል።
በዘርፉ ለተመዘገበበት ስኬት ዋነኛ ምክንያቶች በአገሪቱ የተወሰደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምርትና ምርታማነትን ማሳደጉ፣የገበያ መዳረሻዎች መስፋታቸው እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
እንዲሁም በሕገ-ወጥ የምርት ክምችት ላይ የተደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን መጠን መጨመሩ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የማነጻጸሪያ ዋጋ ተመን በዓለም አቀፍ የገበያ ዋጋ ልዋዋጭነት መሠረት በየወቅቱ ክለሳ በመደረጉ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ከፍተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ዘርፎች ማዕድን (149ነጥብ 4በመቶ)፣ ኤሌክትሪክና ሌሎች (112ነጥብ 3በመቶ)ና ግብርና (90ነጥብ5)በመቶ ናቸው።
እና የማምረቻ (ማኑፋክቸሪንግ)ዘርፎ (87ነጥብ6 በመቶ) አፈጻጸም እንደተመዘገበበት ገልጸዋል ይላል ከሚኒሰቴሩ የተገኘው መረጃ።
ሚኒስቴሩ በቀጥታ ከሚከታተላቸው የወጪ ንግድ ምርቶችም 606ነጥብ8 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ 527ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱን 87 በመቶ ማሳካቱን አስታውቀዋል።
ሚኒስቴሩ ባለፉት ስምንት ወራት፣ የዕቅዱን 110 በመቶ ያስመዘገበበት ከ2ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን መስጠቱ ተገልጿል።
በዚህም 2ነጥብ 4ሚሊዮን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዶ፣ 2ነጥብ6 ሚሊዮን አገልግሎቶችን መስጠት ተችሏል።
ሚኒስቴሩ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ራዕይን እውን ለማድረግ ቀዳሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ሲሆን፤ የዘረጋው የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰራር የንግዱ ማህበረሰብ ጊዜውን፣ ጉልበቱንና ገንዘቡን ሳያባክን ባለበት ቦታ ሆኖ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደተቻለ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።
በተጨማሪም የዲጂታል አገልግሎት ሽፋኑን ለማሳደግ፣ የወጪ ንግድ የኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን መሰጠት መጀመራቸው ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማኒስቴር
ወጪ ንግድ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!