እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:11:28 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጉባዔን ታስተናግዳለች

2 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጉባዔን ታስተናግዳለች
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ በተለይም የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መቀመጫ እንደሆነች በየዓመቱ የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባዔን ጨምሮ በርካታ ስብሰባዎችን ታስተናግዳለች፡፡

በተለይም ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ወትሮም የዓለም አራተኛ የዲፕሎማሲ መዲናዋ የምታስተናግዳቸው እንግዶች ቁጥር ጨምሯል፡፡

በዚያው ልክ የምታስተናግዳቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎች በዚያው ልክ እየተበራከቱ ሄደዋል፤ባለፈው ዓመት ብቻ 150ስብሰባዎች መስተናገዳቸው ሳይረሳ፡፡

አሁን ደግሞ ተራው የዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS)ሆኗል፡፡
ማህበሩ ኢትዮጵያ 89ኛውን ጉባዔውን በሚቀጥለው ዓመት እንድታስተናግድ በመምረጡ፡፡

ኢትዮጵያ ጉባዔውን እንድታስተናገድ ወሳኝ ሚና የተጫወተው የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መሆኑም ተገልጿል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው መንግሥት ለስፖርት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት እና እየገነባ ባለው መሠረተ ልማት ስፖርታዊ ሁነቶችና ኮንፈረንሶች ወደ ኢትዮጵያ እያመጣ መሆኑን  አመልክቷል።

በሉዛን፤ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 88ኛው ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ  ቀጣዩን ጉባዔ በይፋ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።

ይህ ታላቅ ስኬት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኩራት ከመሆኑም በላይ፣ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ዕድልንም ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማመላከት።

ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሚሆነው ጉባዔ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ባደረገው ስልታዊ ጥረትና መንግሥት በሰጠው ድጋፍ የተገኘ  ውጤት መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ይህን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ለማስተናገድ መመረጧ የአገሪቷን የዲፕሎማሲያዊ ብቃትና የሚዲያ ማዕከልነት በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም የሚያረጋግጥ ነው  ብሏል።

በተለይም መንግሥት በየደረጃው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞችንና ሁለንተናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት እያከናወነ ያለውን ተግባርና ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳየት  ዕድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ መስተናገዳቸው፥ በስፖርቱ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ፣ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት የበለጠ ለመግለጥ እንዲሁም ለእገር ውስጥ ባለሙያዎች  የልምድ ልውውጥ ለመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።

ይህም መንግሥት ስፖርቱን የሰላምና የልማት ምሰሶ ለማድረግ ለሚያደርገው ጥረት ተጨማሪ አቅምና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።


ስፖርትገጽታ ግንባታ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!