እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:30 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ኢትዮጵያ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ግራንድ ፕሪ

3 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ግራንድ ፕሪ

ኢትዮጵያ በዚህ ሣምንት ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ታስተናግዳለች፡፡

ውድድሩ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1985 እስከ 2009 በቀድሞው ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን ግራንድ ፕሪ በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረ ሲሆን፣ አትሌቶች በየውድድሩ ነጥብ እየሰበሰቡ በዓመቱ መጨረሻ ለሚካሄደው የግራንድ ፕሪ ፍፃሜ የሚበቁበት ሥርዓት ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ይህ ሥርዓት በዳይመንድ ሊግና በአህጉራዊ(ኮንቲኔንታል) ቱር ተተክቷል።

አዲስ አበባ በዚህ ሣምንት የምታስተናግደው በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ አደረጃጀት የአንድ ቀን ግራንድ ፕሪ ተብሎ የሚጠራ ውድድር ነው፡፡

ውድድሩ በአንድ ቀን ውስጥ ተከታትለው በሚከናወኑ የትራክና የሜዳ ተግባራት የሚጠናቀቅ የሊግ ውድድር ዓይነት ነው።

በዋናነት  የዓለም አትሌቲከስን ውድድሮችን በሚያዘጋጀው ወርልድ አትሌቲክስ የሚከናወኑ አህጉራዊ  ወድድሮች ሥ የሚካሄዱ መሆናቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

አትሌቶች ለታላላቅ የዓለም ሻምፒዮናዎችና ለኦሎምፒክ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ ነጥብ እንዲሰበስቡና የሙያ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል መሰጠት የውድድሩ ዓላማ ነው።አትሌቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ደረጃቸውን ለማሻሻልና የገንዘብ ሽልማት ለማግኘትይሳተፉበታል።

በውጤት ጥራትና በሽልማት መጠን ላይ ተመስርቶየሚዘጋጁ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ተቋም የአህጉራዊ ግራንድ ፕሪ ውድድሮች በአራት ዋና ደረጃዎች ይከፈላሉ። ለነዚህ ውድድሮች ደረጃ የሚወሰነው በሽልማት መጠን፣ በውድድሩ ጥራትና በሚያስገኙት የደረጃ ነጥብ ላይ ተመስርቶ ነው።

ከነዚህም በወርቅ  ደረጃ የሚሰናዳው ከዳይመንድ ሊግ ቀጥሎ ከፍተኛው የአንድ ቀን ውድድር ደረጃ ነው።ቀሪዎቹ በብር በነሐስና ቻሌንጀር ተብለው  የተመደቡ ናቸው።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ የሆነው የነሐስ ደረጃ ያለው ውደድር  የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በወርቅ ደረጃ የሚካሄደው ውድድር አጠቃላይ የሽልማት ገንዘብ ቢያንስ 200ሺህ ዶላር  ሊኖረው የሚገባ ሲሆን፣ ለዋና ውድድሮች ቢያንስ 10ሺህ ዶላር ሽልማት ይሰጣል።

ለተሳታፊዎች ምድብ "ኤ" ከፍተኛ ነጥብ ያስገኛል።ቢያንስ ሦስት ተወዳዳሪ አትሌቶች ከዓለም 50 ምርጥ ደረጃ ውስጥ መገኘት አለባቸው።

የብር ደረጃ ያለው ውድድር በየአህጉሩ የሚገኙ የአትሌቲክስ ማህበራት የሚመሩት አጠቃላይ የሽልማት  መጠኑ ቢያንስ 75ሺህ ዶላር ሊኖረው የሚገባ ውድድር ነው ።

በእያንዳንዱ ውድድር ቢያንስ አምስት ሺህ ዶላር ሽልማት ሊኖረው የሚገባው ይህ ውድድር፣ የምድብ  "ቢ" ነጥብ ያስገኛል።

በውድድሩ ከዓለም 100 ምርጥ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ቢያንስ ሦስት አትሌቶች መሳተፍ አለባቸው። ለታዳጊ አትሌቶችና ለአዳዲስ አዘጋጅ አገሮች  ድል የሚሰጠው የነሐስ ደረጃ የተሰጠው ውድድር  መሆኑንም መረጃው ያሳያል።

ለውድድሩ የሚመደበው አጠቃላይ የሽልማት ገንዘብ ቢያንስ 25ሺህ ዶላር ሊኖረው ይገባል።የዚህ ውድድር ምድብ  "ሲ" ነጥብ ነው። ቢያንስ ሦስት አገሮች የተውጣጡ ስድስት አትሌቶች መወዳደር አለባቸው።

ቻሌንጀር የተባለው ንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2022 የተጀመረ አራተኛውና የመግቢያ ደረጃ ያለው ውድድር ነው።

በዚህ ውድድር ለሚካፈሉ  የሚሰጠው በአጠቃላይ 20ሺህ ዶላር  ያላነሰ ሽልማት ይሰጣል።

የዚህኛው ውድድር ዓላማ አነስተኛ አቅም ላላቸው አዘጋጆችና በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች ዓለም አቀፍ  ልምድ እንዲቀስሙ የታለመ ነው።

የዓለም አትሌቲክስ በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት 11 የወርቅ ደረጃ ያላቸወን ውድድሮች በማካሄድ ላይ ነው፡፡ከነዚህም በሜልቦርን፣ አውስትራሊያ የተዘጋጀው ባለፈው ወር ተከናውኗል፡፡ቀጣዩ ውድድር በያዝነው ወር ናይሮቢ፣ ኬንያ ይካሄዳል፡

ጃፓን፣አሜሪካና የአውሮፓ አገሮች ደግሞ 10 ውድድሮችን ከግንቦት እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ እንደሚያካሂዱ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያሳያል፡፡

አዲስ አበባ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ቀን ግራንድ ፕሪ የነሐስ ደረጃ ውድድርን ሚያዝያ 10 ቀን 2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም ታስተናግዳለች።

ውድድሩ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን የምታሰተናግድበትን አቅምና ልምድ ለማሳደግ እንደሚረዳት ታምኖበታል፡፡በውድደሩ የሚሳተፉ አትሌቶች በመታወቅ ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድሩ የሚካፈሉ አትሌቶችንና የሚሳተፉባቸውን የውድድር ዓይነቶች መረጃ በመስጠት ላይ ነው፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውድድሩን በብቃት ለማስተናገድ ሁለንተናዊ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን አስታውቋል፡፡

አገሪቱ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ከማሰናዳት ያላለፋትን ልምድ ወደተሻለና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ወደምታስተናግድበት ደረጃና አቅም ያስችላታል ተብሎም ይታሰባል፡፡

በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብፅ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሌሶቶ፣ ኦማንና ሳዑዲ ዓረቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሳሳይ ውድድሮችን ያዘጋጃሉ።

በተጨማሪም የዓለም አትሌቲክስ ሪሌይ በጋቦሮኒ፣ ቦትስዋናና የመክፈቻው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮና) በቡዳፔስት፣ ሐንጋሪ ይደረጋሉ።

 

 

 

ስፖርትአትሌቲክስየአንድ ቀን ግራንድ ፕሪ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!