እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:38 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:38 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መድረክ ታስተናግዳለች
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
የካቲት 28/2018
ኢትዮጵያ ስምንተኛውን የአፍሪካ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መድረክ በሚያዝያ ታስተናግዳለች።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ያዘጋጀው ፎረም “ አጀንዳ 2030 እና አጀንዳ 2063ን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ዲጂታል ኢኖሼሽን ውጤታማ ማድረግ” በሚል መሪ ሐሳብ ይካሄዳል።
በዚህም መድረኩ ከሚያዝያ 18-19/2018 ውድድር አበባ ከተማ
እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡
መድረኩ የአፍሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ኢኖቬተሮችና የልማት አጋሮችን ያገናኛል።
ባለድርሻዎቹ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያለውን ሚና አስመልክቶ ይመክራሉ።
መድረኩ የአፍሪካ የኢኖቬሽን አጀንዳን የሚያራምድ ቁልፍ ማዕቀፍ ሆኖ እንደሚያገለግል የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።
በመንግሥቭ፣ በአካዳሚክ ማህበረሰቡ፣ በኢንዱስትሪና ዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይም ውይይት ይደረጋል።
አፍሪካ በዘላቂ ልማት ግቦች የደረሰችበትን የአፈጻጸም ደረጃ በመድረኩ ይገመግማል።
ውሃን ንጽህና፣ ተመጣጣኝና ንጹህ ኢነርጂ፣ ኢንዱስትሪና መሠረተ ልማት፣ ዘላቂ ከተሞችና የልማት አጋርነት ጨምሮ ዘላቂ ልማት ግቦችን የተመለከተ ውይይትም ይካሄዳል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ኢኖቬሽን ተኮር መፍትሄዎች ጅና ቀጣናዊ ትብብርን በሚያጠናክሩ የተግባር እርምጃዎች ላይ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ።
ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ከፍተኛ አዎንታዊ ለውጥ ያመጡ ቴክኖሎጂዎች፣ ጀማሪ ሥራ ፈጠራዎች (Start Ups)፣ የምርምር ኢኒሼቲቮችና የኢኖቬሽን ማዕከላት ሥራዎች ለእይታ ይቀርባሉ።
የዕውቀት ሽግግርን ለማሳለጥ፣ በዩኒቨርሲቲዎችና ምርምር ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት ማጠናከር እንዲሁም በአፍሪካ ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመደገፍ ያ
ስችላል
ብሏ
ል ኮሚሽኑ።
በመድረኩ የአህጉሪቱ መንግሥታት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የአፍሪካ ልማት ባንክ አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የትምህርት ተቋማትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Addis Ababa
1
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!