እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:09:36 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:09:36 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ስፖርት
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፓሪስና በብራዚሊያ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
1 / 2
በሣምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
ከነዚህም ዛሬ የፓሪስ ማራቶን ውድድር አትሌት ሹሬ ደምሴ አሸንፋለች።
ሹሬ ርቀቱን 2 ሰዓት 18 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
አትሌት ምስጋኔ አለማየሁ ርቀቱን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት በውድድሩ ሁለተኛ ሆናለች።
አትሌት እናትነሽ አላምረው ደግሞ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ፈጽማለች።
በወንዶች ምድብ ጣሊያናዊው አትሌት የማነብርሃን ክሪፓ 2 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል።
የማነብርሃንን በመከተል አትሌት ባየልኝ ተሻገር 2 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ በመሆን ፈጽሟል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ርምጃ ውድድር የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ በአትሌት ምስጋና ዋቁማ አግኝታለች።
በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የእርምጃ የቡድን ሻምፒዮና ላይ በወንዶች የእርምጃ ግማሽ ማራቶን የተወዳደረው ምስጋና ዋቁማ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡
ውጤቱ በኢትዮጵያ የእርምጃ ውድድሮች ተሳትፎ ታሪክ የመጀመሪያውን የዓለም አቀፍ ውድድር የተገኘ ድል መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡
አትሌት ምስጋና ውድድርሩን ያጠናቀቀው በአንድ ሰዓት ከ27:33 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓት ነው፡፡
በሴቶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ህይወት አምባው ዘጠነኛ፤በዚሁ ርቀት የተወዳደረው
አብዱሰላም አብዱልወሀብ 11ኛ ወጥቷል፡፡
ስፖርት
አትሌቲክስ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!