እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:38 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ኢትዮጵያውያን የጎዳና ላይ ውድድሮችን አሸነፉ

1 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያውያን የጎዳና ላይ ውድድሮችን አሸነፉ
Tsige
1 / 3
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሣምንቱ መጨረሻ በተደረጉት የጎዳና ላይ ሩጫ ወድድሮች አሸነፉ።

ከውድድሮቹ መካከል በፖርቱጋል ርዕሰ ከተማ ሊዝበን የተደረገውን የግማሽ ማራቶን  ውድድር ጽጌ ገብረሰላማ በበላይነት አጠናቃለች፡፡

ጽጌ በከተማዋ የተካሄደውን ውድድር በተከታታይስታሸንፍ የእሁኑ ለሁለተኛዋ ጊዜ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል።

ጽጌ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1:04.48 ሲወስድባት፥ በውድድሩ የተሳተፈችው ግርማዊት ገብረ እግዚአብሔር በ1:07.30 በመግባት አምስተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቃለች።

በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የተደረገውን ተመሳሳይ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፍታው ዘርዓይ በቀዳሚነት በመግባት አሸንፋለች።

አትሌቷ የገባችበት 1:05.12 የቦታው ምርጥ ሰዓት መሆኑም ተገልጿል።

በጃፓን ናጎያ ሴቶች ማራቶን ዳግም ዓይናለም ደስታ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ውድድርን እጠናቃለች፡፡

ውድድሩን በ2:22:37 በማጠናቀቅ።

ዓይናለም በአምስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በማራቶን መወዳደሯ ተመላክቷል።

Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!