እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:16 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

ከአራት ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ኮኬይን ከነአዘዋዋሪው ተያዘ

1 ደቂቃ ንባብ
ከአራት ኪሎ ግራም  በላይ የሚመዝን ኮኬይን ከነአዘዋዋሪው ተያዘ
ኮኬይኑ መነሻውን ናይጄሪያ መዳረሻውን ሕንድ ባደረገው ተጠርጣሪ ሻንጣ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ምክሮ ነበር ።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 4 ነጥብ 48 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕጽ ሊያሳልፍ የሞከረ አንድ ናይጀሪያዊ ተጠርጣሪ መያዙን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገለጸ።

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው፤ መነሻውን ሌጎስ፤ናይጄሪያ መዳረሻውን ሕንድ ባደረገው ተጠርጣሪ ሻንጣ ውስጥ ተደብቆ ሊያልፍ የነበረውን  የሚመዝን ኮኬይን ይዟል።

የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ሠራተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው ባደረጉት ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ  ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

ይኸው 172 ፍሬ ብዛት ያለው  አደገኛ ዕፅ በዓለም አቀፍ  መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በተገጠመ  ዘመናዊ ኤክስሬይ መሣሪያ መለየቱንም አመልክቷል።

አገልግሎቱ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ተጠርጣሪውና ሌሎች መረጃዎች ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ማስተላለፉንም ገልጿል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ኮኬይን ጨምሮ አደገኛ ዕጽ ለማስተላለፍ የሚሞክሩ ሰዎች በየጊዜው በቁጥጥር ሥር ይውላሉ፡፡


አደገኛ ዕጽ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!