እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:43:13 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የሆርሙዝ ወሽመጥ ለንግድ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ክፍት ሆነ

2 ደቂቃ ንባብ
የሆርሙዝ ወሽመጥ ለንግድ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ክፍት ሆነ
ኢራን የምትቆጣጠረውና የዓለም 20 በመቶ የንግድ መተላለፊያ መሥመር የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ በመዝጋቷ በተለይ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶችን ለማግኘት ችግር ተፈጥሮ ቆይቷል።
ሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ የዓለምን ሕዝብ ሲያስጨንቅ ውጥረት ሲፈጥር የነበረው የነበረው የሆርሙዝ ሰርጥ ዛሬ ተከፍቷል።

አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ ለስድስት ሣምንታት ያህል የተዘጋው።በሁለቱ ወገኖች በጋራና በተናጠል የተከፈተው ጦርነት አድማሱን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮችም ተሰፋፍቷል።

ኢራን የምትቆጣጠረውና የዓለም 20 በመቶ የንግድ መተላለፊያ መሥመር የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ በመዝጋቷ በተለይ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶችን ለማግኘት ችግር ተፈጥሮ ቆይቷል።

በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገሮች ምርቶቹን ለማስገባት ባለመቻላቸው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት አስከትሎባቸዋል።

በአዲስ አበባና በአህጉሪቱ ታላላቅ ከተሞች ነዳጅ ለመቅዳት ረጃጅም ሰልፎች በነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ማየትና አንዳንዴም በተሽከርካሪዎች ውስጥ ማደር የተለመደ መስሎ ነበር።

ዛሬ የተሰበረው ዜና ቅድመ ኢራን ጦርነት የነበረውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ይመልሰዋል ተብሎ ባይታመንም፤ለጊዜው ግን እፎይታ የሚሰጥ እንደሆነ ብዙዎችን ያስማማል።

በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትሰስር ገጻቸው እንዳስታወቁት በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ንግድ መርከቦች እንዲያልፉ ሙሉ ለሙሉ ክፍት ተደርጓል።

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሸመጥን መተላለፊያ ሙሉ በሙሉ ለንግድ መርከቦች ክፍት ሆኖ ለጉዞ ዝግጁ በመሆናቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሰርጡ ላይ ተጥሎ የነበረው የባህር ላይ እገዳ በመነሳቱ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ጀምረዋል።ይህንንም ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የነዳጅ ዋጋ 10ከመቶ ቀንሷል።

በዚህም ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ11 ነጥብ 5 በመቶ በመቀነሰ በበርሜል 84 ዶላር ገደማ ተሸጧል። የብሬንት ድፍድርፍ ነዳጅ በበርሜል 88 ዶላር ሲሸጥ፣ያሳየው ቅናሽ 11 በመቶ ያህል መሆኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመዘገብ ላይ ናቸው ።

የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማን የያዘችው "ሻላማር" የነዳጅ ጫኝ መርከብ እገዳው ከተነሳ በኋላ ሰርጡን ያለፈች የመጀመሪያዋ መርከብ ሆናለች።

ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶቾ 450ሺህ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ  በመጫን ወደ ካራቺ  እየተጓዘች ነው።

ሰርጡ በመከፈቱ  ተስፋ ሰጪ እርምጃ ቢሆንም፣በሰርጡ 823 የሚጠጉ መርከቦች ስለሚገኙ ሁኔታው ወደቀደመው ደረጃ ለመመለስ ጊዜ መጠየቁ እንደማይቀየር መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሰርጡ መከፈት የዓለም የፋይናንስ ማዕከላትና የአክሲዮን ገበያዎች መነቃቃት ታይቶባቸዋል፣ በተለይም በአውሮፓ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንደጨመረም ዘገባዎች አመልክተዋል። 
ኢኮኖሚየነዳጅ ቁጥጥር

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!