እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:45 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በረራዎች በአብዛኛው እንደተስተጓጎሉ ናቸው

2 ደቂቃ ንባብ
የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በረራዎች በአብዛኛው እንደተስተጓጎሉ ናቸው
disruptions 01
1 / 3

በመካከለኛወ ምሥራቅ አገሮች በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ የተቋረጡ በረራዎች በአብዛኛው እንደተስጓጎሉ ቢሆንም፤አንዳንድ አየር መንገዶች ውሱን በረራዎችን ማድረግ ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛወ ምሥራቅ አገሮች በመቋረጡ ገቢው  እንደሚቀንስበት ለቢቢሲ መግለጹ ይታወሳል፡፡


ባለፈው ሣምንት አሜሪካና አሥራኤል ከኢራን ጋር በተፈጠረ ግጭት  የበረራ መሥመሮች በመዘጋታቸው ከ10ሺሀ በላይ የአውሮፕላን ጉዞዎች መቀጠል አልቻሉም፡፡

 በዚህም ከአገሮቹ ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎችና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ወደ አገሮቹ  የሚደረጉ በረራዎች በአብዛኛው ቆመዋል፡፡

 በተለይም የአውሮፓና የሰሜን አየር መንገዶች ወደ አገሮቹ የሚያደርጓቸውን በረራዎች ሙሉ በሙሉ መቋረጣቸውነ መሆናቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚህም በዋነኝነት ወደ ዱባይ፣አቡዳቢ፣ዶሃና ቴል አቪቭ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች ተሰርዘዋል፡፡

ሆኖም የኳታር አየር መንገድ ወደ ፓሪስ በረራ መጀመሩን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶቹ ኢሚሬትስና ፍላ ዱባይ አየር መንገዶች ወደ ዱባይ፣አቡዳቢና ሻርጃህ ከተሞች በረራዎችን ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

ሚድ ኢስት አየር መንገድ ከቤይሩት ወደ ለንደን፣ፓሪስ፣ፍራንክፈርትና ጂዳ ከተሞች እያደረገ መሆኑንም ከዘገባዎቹ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በውሱን ደረጃ የተጀመሩት በረራዎች በግብጽ ወይም በተርኪዬ አየር ክልል ላይ ስለሚካሄዱ አየር መንገዶቹ ከሁለት እስከ ስድስት ሰዓት ተጨማሪ በረራ ለማድረግና መንገደኞችም ተጨማሪ ወጪ ለማውጣት መገደዳቸውም ተመላክቷል፡፡

በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የተከሰተው ግጭት በመቀጠሉ በረራዎች ወደ መደበኛ ሥርዓታቸው ለመመለስ ጊዜ ስለሚወስድ አየር መንገዶቹ ለኪሳራ መጋለጣቸው የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ በየቀኑ በርካታ በረራዎች ስለሚያካሂድ በገቢው ላይ  ተጽዕኖ እንደሚያሳድርበት አስታውቋል፡፡

 በሣምንት ከ45 እስከ 50 ሺህ መንገደኞችና የዕቃ ጭነት ተደምሮ ወደ 160 በረራዎች ስለሚሰረዙ ገቢውን እንደሚቀንስበት አመላክቷል።

 

Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!