እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:55 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:40:55 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ምርጫ 2018
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 አራዝሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 አራዘመ።
የቦርዱ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28ቀን 2018ዓ.ም እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያከናውን ማሳወቁ ይታወሳል።ቦርዱ የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማከናወን ባወጣው ዕቅድ መሠረት በአሁኑ ወቅት የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቋል።በጊዜ ሠሌዳው መሠረት የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣በዚህ ሂደት ውስጥ፦
በተያዘው ዕቅድ መሠረት በተወሰኑ አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የኔት-ዎርክ አቅርቦት እና በምዝገባ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በፍተሻ እየለዩ ሲስተሙን አስተማማኝና ቀልጣፋ ለማድረግ ሂደቱ የጠየቀውን ጊዜ ማካካስ በማስፈለጉ፣
የኔት-ዎርክ አቅርቦታቸው አስተማማኝ ነው ተብለው የቀረቡ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የኔት-ዎርክ አቅርቦት አለመኖሩ በተጨባጭ በመታየቱ ወደ ማንዋል በመቀየር ሂደት ለባከነ ጊዜ ማካካሻ በማስፈለጉ እና
በተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በትራንስፖርት አቅርቦት ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ በወቅቱ ባለመድረሳቸው የተፈጠረውን የመራጮች ምዝገባ መዘግየት ማካካስ አስፈላጊ በመሆኑ ቦርዱ የመራጮችን የምዝገባ ሁለት የበዓል ቀናትን ሳይጨምር እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018ዓ.ም አራዝሟል።
የመራጮች ምዝገባ መራዘም
ምርጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ምርጫ 2018
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!