እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:36 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለተወሰኑ በረራዎች መሥመሮችን ክፍት አድርጋለች

2 ደቂቃ ንባብ
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለተወሰኑ በረራዎች መሥመሮችን ክፍት አድርጋለች
በረራ መሥመሮች

አዲስ አበባ የካቲት 28 ቀን 2018

የአቡዳቢው ዛይድ ዓለም አቀፍና የዱባይ አቪዬሸን በመካከለኛው  ምሥራቅ አገሮች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ

ያልወጡ የውጭ ዜጎችን   በከፊል ለማስወጣት ዝግጅት ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡

የአቡዳቢ ሚዲያ ጽሀፈት ቤት እንዳረጋገጠው፤በአካባቢው አገሮች በተከሰተው ጦርነት ከአገሪቱ መውጣት ለሚፈልጉ

ዜጎች የተወሰኑ በረራዎች የተፈቀዱት የአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜና ሌሎች አፋጣኝ አገልግሎት ክፍሎች ማዕከል

በፈጠሩት ቅንጅት ነው፡፡                     

ቅንጅቱ በፈቀደው መሠረትም  ‹‹በጣም አስፈላጊ›› ተብለው ለተለዩ ጉዳዮች ከአገሪቱ መውጣት ያለባቸው የውጭ

ዜጎች በሚፈቀዱላቸው በረራዎች እንዲወጡ ይደረጋል፡፡

በዚህም ከአገሪቱ በየሰዓቱ ለ48 በተመረጡ መሥመሮች እንደሚከናወኑ የአገሪቱ ሲቪል አቪዬሸን በሚያዘጋጀው

መሠረት እንደሚከናወኑም አስረድቷል፡፡

በረራዎቹ የተፈቀዱት በበረራዎች መስተጓጎል ሳቢያ ከአገሪቱ መውጣት እየፈለጉ መውጣት ያልቻሉትን የውጭ

 ዜጎችንና ወደ አገሪቱ ገብተው መውጣት ያልቻሉትን መንገደኞች ወደ መዳረሻቸው ለማድረስ መሆኑን መረጃው

ያመለክታል፡፡ 

ኢት አሃድና ኢሚሬትስ የተባሉ አገሪቱ አየር መንገዶች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት መደበኛ አገልግሎት በአብዛኛው የተሰተጓጎለ ቢሆንም፤ ለመንገደኞቹ የተለየ አገልግሎት ለመሰጠት ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጸዋል፡፡

ኢት አሃድ አየር መንገድ ከአቡዳቢና ወደ አቡዳቢ የሚደረጉ በረራዎች እስከ ዛሬ ዕኩለ ቀን ቢያቆምም፤ሆኖም

በተለየ ሁኔታ የተመረጡ ፣የጭነትና የውጭ ዜጎችን ለማወጣት በረራዎች እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡

ኢሚሬትስ አየር መንገድ በበኩሉ ወደ ዱባይ የሚደረጉ በረራዎችን እስከ ነገ ድረስ በማቆም ትኩረቱን አሰቀድመው 

የአየር መንገዱን ቲኬት ቆርጠው በረራቸው ለተረጋገጠላቸው ቅሚያ በመሰጠት  እንደሚያስተናግዳቸው

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ለተወሰኑ በረራዎች መሥመሮችን ክፍት አድርጋለች

አስረድቷል፡፡

ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያዎች መጨናነቅ እንዳይፈጠርና ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ለማገልገል የበረራ

ጊዜና የሚሳፈርቡት አየር መንገድ የሚያረጋግጥ የተለየ መልዕክት እስኪደርሳቸው በትዕግሥት እንዲጠባበቁ

ማሳሳቢያ ተሰጥቷል፡፡

የአገሪቱ መንግሥት በአካባቢው አገሮች በተፈጠረው ግጭት ከአገሪቱ መውጣት ያልቻሉ መንገደኞች ድጋፍ

እንደሚያደርግ ያመለከተው መረጃ፣መንገደኞቹ በሆቴል የሚቆዩበት፣ሕክምና የሚያገኙበትና መንግዶን ያካተተ ልዩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በቀጣናው አገሮች የተከሰተወ ቀውስ ቀሰ በቀሰ እስኪቃለል አገሪቱ በአቪዬሸን ዘርፍ ባላት ወሳኝ ሚናና

የዘርፉ ተዋንያንን ደህንነት በማሰጠበቅ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ አረጋግጣለች ይላል ዘገባው፡፡

 

United Arab Emirates

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!