እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:20 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:20 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
የአልዛይመር ምልክቶችን በአንድ ደቂቃ መለየት ተቻለ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
አልዛይመር የሰውን ልጅ የማስታወስና የማሰብ ችሎታ በመቀነስ የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤን የሚያዛባ በሽታ ነው ፡፡
1 / 2
አልዛይመር የሰውን ልጅ የማስታወስና የማሰብ ችሎታ በመቀነስ የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤን የሚያዛባና በተለይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሕመም ነው።
የአሜሪካ ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የአልዛይመር በሽታ ምልክቶችን በአንድ ደቂቃ ውስጥ መለየት ተችሏል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ቴክኖሎጂው ሰዎች በቃላት ምርጫቸው፣ በንግግር ፍሰታቸውና በዐረፍተ ነገር አወቃቀራቸው ላይ የሚያሳዩዋቸውን ለውጦች መሠረት በማድረግ የመለየት አቅም አለው።
በተለምዷዊው መንገድ የሚካሄዱ የአልዛይመር ምልክት ምርመራዎችን ይተካል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እጅግ ቀላል፣ ፈጣንና ለአጠቃቀም ምቹ መሆኑም ተነግሮለታል።
እስካሁን በሕክምናው ዘርፍ ለአገልግሎት እየዋሉ ያሉ የአልዛይመር መመርመሪያ ዘዴዎች ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ከመሆናቸውም በላይ፣ አልፎ አልፎ በባለሙያዎች የግል ምልከታ ላይ የሚመሰረቱ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል።
አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታው አስቀድሞ እንዲታወቅና አስፈላጊው ሕክምና በወቅቱ እንዲጀመር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የሳይቴክ መረጃ ያመላክታል።
በዓለም ዙሪያ በዚህ ሕመም የሚጠቁ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል፡፡
በአሜሪካ ብቻ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሕሙማን እንዳሉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት
ጤና
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአልዛይመር በሽታ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!