እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:48 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያስገኘ ነው

2 ደቂቃ ንባብ
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያስገኘ ነው
ኢትዮጵያ የደን ጭፍጨፋ በኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተፅዕኖ በመረዳት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነድፎ በሕዝብ ንቅናቄ እየተገበረ ይገኛል፡፡

በዓለም በየዓመቱ በሚፈጸም የደን ጭፍጨፋ ከፍተኛ ውድመት እንደሚደርስ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የምድራች ሳንባ በሚባለው የአማዞን ጫካ በሚደርስበት ጉዳት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱ ይሰማል፡፡

በአፍሪካም የተሻለ የደን ይዞታ አለባቸው በሚባሉ በምድረ ወገብ አካባቢ ባሉት ደን ይዞታዎች ላይ የሚደርሰው ጥፋት አሳሳቢ ከሚባል  ድረጃ ከደረሰ ሰነባብቷል፡፡

በኢትዮጵያም በደን ሀብት ለይ ተመሳሳይ ችግሮች ስለነበሩ ሀብቱ መሳሳትና ወደ መጥፋት ደርሶ ተብሎ ስጋት ተጋርጦ ነበር፡፡የደን ይዞታው ውሱን በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች ብቻ ተወስኖ የቀረበት ሁኔታ መፈጠሩ፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመቀልበስ የሚያስቸሉ ሥራዎች አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ባለፉት ሰባት ዓመታት በመከናወናቸው አመርቂ ውጤቶች ለመመዘገብ በቅተዋል፡፡

በዚህም ከ48 ቢሊዮን በላይ የደን፣ምግብ ነክና ቋሚ ተክሎች በመትከል ሕዝቧን ተጠቃሚ አድርጋለች፡፡አገሪቱ ያደረገቸው እንቅስቃሴም አድናቆት ተችሮታል፡፡

በያዘነው ክረምትም ለስምንተኛ ዓመት በተመሳሳይ መንገድ ተከላ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች ነው፡፡

የዓለም የደን ቀን ለ14ኛ ጊዜ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ዛሬ አክብረዉታል፡፡

የበዓሉ መሪ ሐሳብ ደግሞ “ደን እና ምጣኔ ሃብትነው፡፡

 የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በበዓሉ ደን የዓለም ኢኮኖሚ መሠረትና የአንድ ሦስተኛው ሕዝብ የኑሮ መሠረት እንደሆነተናግረዋል፡፡

ዓለም  በደን ጭፍጨፋ ሳቢያ በየዓመቱ 4 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት እንደምታጣ የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ጥናትእንደሚያመላክት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የደን ጭፍጨፋ በኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተፅዕኖ በመረዳት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነድፎ በሕዝብ ንቅናቄ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡

 መንግሥት ለተፈጥሮ ሃብት ልማት በሰጠው ትኩረት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ባለፉት ስምንት ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ 48 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ይህም የደን ሽፋኑን ከ17 ነጥብ 3 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ይማም በአገሪቱ በተቀናጀ የደን ልማት የደን ጭፍጨፋን በአማካይ 92 ሺህ ሄክታር ወደ 27 ሺህ ሄክታር መሬት ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዓለም የደን ሃብት 1 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ የሚሆነው ሕዝብ  የኑሮ መሠረት መሆኑን አመልክተው፣ከደንም ለምግብ ዋስትና፣ ለመድኃኒት ግብዓትነትና  ገቢ በማመንጨት የሚያስገኘው ገቢ ቀላል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ 

አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብርግብርና

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!