እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:50 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የአንድ አሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 157.46 ብር ሆኗል

1 ደቂቃ ንባብ
የአንድ አሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 157.46 ብር ሆኗል
በዚህ የ70 ሚሊየን ዶላር ጨረታ በቀረበበት ጨረታ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 157.46 ብር ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 21ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ዛሬ አካሂዷል፡፡

በዚህ የ70 ሚሊየን ዶላር ጨረታ በቀረበበት ጨረታ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 157.46 ብር ሆኗል፡፡

በዕለቱ በጨረታ የተገበያያ የዶላር መጠን 70 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡

ባንኮቹ በጨረታ ወቅት ለመግዛት ያሳዩት የዶላር ፍላጎት መጠን 241.52 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ባንኩ አስታውቋል፡፡

በጨረታው ለአንድ ዶላር የቀረበ ከፍተኛ ዋጋ ብር 158.50ብር ሲሆን፥ለአንድ ዶላር የቀረበ ዝቅተኛ ዋጋ ብር 154.50 ብር ያቀረቡ ነበሩ፡፡

አማካይ የዕለቱ የግብይት ለአንድ ዶላር ዋጋ ብር 157.46 ብር ሆኗል፡፡

በጨረታው ላይ የተሳተፉ 30ባንኮች ሲሆኑ፥በጨረታ ዶላር የደረሳቸው ባንኮች ዘጠኝ እንደሆነ መረጃው ያመለክታል፡፡

የካቲት 24/2018 በተካሄደው የ20ኛ ዙር 70 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አማካይ ዋጋ 155.94 ብር ነበር፡፡

በዚያው ወር አጋማሽ ላይ በተካሄደው የ19ኛ ዙር 500 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አማካይ ዋጋ 153.25 ብር፤የካቲት 10 በነበረው ጨረታ በአማካይ ዋጋ 155.12 ብር እንደነበርም ተመላክቷል፡፡



የውጭ ምንዛሪየውጭ ምንዛሪ ጨረታየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!