እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:45:45 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚዎች ታወቁ

2 ደቂቃ ንባብ
 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚዎች ታወቁ
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚዎች በተደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ተለይተዋል።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚዎች ባለፉት ቀናት በተደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ተለይተዋል።

በዚሁ መሠረት ሪያል ማድሪድ ከባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ፒ ኤስ ጂ ከሊቨርፑልና ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ።

ትናንት በተካሄዱት የሊጉ ሦስት የመልስ ጨዋታዎች የሩበ ፍጻሜ ጨዋታዎችን ለመለየት አሰችለዋል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል ጋላታሳራይን 4 ለ 0 ረቷል።

ዶምኒክ ስቦዝላይ፣ ሁጎ ኢኪቲኬ፣ ራያን ግራቨንበርችና መሐመድ ሳላህ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸወ።
 
ሊቨርፑል በደርሶ መልስ ውጤት 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ባየር ሙኒክ አትላንታን 4 ለ 1 በማሸነፍ  ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ ክለብ ሆኗል።

በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን በጨዋታ እና ፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሌናርት ካርልና ሉዊስ ዲያዝ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

 ላዛር ሳማርድዚች ለአትላንታ ብቸኛውን ግብ ማስቆጠሩ ተመላክቷል።

ባየር ሙኒክ በአጠቃላይ ውጤት 1ዐ ለ 2 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲዬም በተካሄደው ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ አትሌቲኮ ማድሪድን 3 ለ 2 ረቷል።
 
 ዣቪ ሲመንስ በጨዋታና በፍጹም ቅጣት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ አንድ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።
 
ለአትሌቲኮ ማድሪድ ግቦቹን ጁሊያን አልቫሬዝ ና ዴቪድ ሃንኮ ናቸው።
 
አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር ውጤት 7 ለ 5 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል።

ባርሴሎና ኒውካስትል ዩናይትድን 7 ለ 2 በማሸነፍ በድምር ውጤት 8 ለ 3 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
 
የሊጉ ሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር  ጨዋታ መጋቢት 29 እና 30  የመልሰ ጨዋታዎች ደግሞ ሚያዝያ 6 እና 7 ቀን 2018 ይደረጋሉ።

ስፖርትእግር ኳስየአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!