እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ኢኮኖሚ
የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ፕሮጀክቱ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተሻሻለ የእንስሳት ልማት፣ የኢኮኖሚ አካታችነትና ጠንካራ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ለውጥ ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
1 / 3
እትዮጵያ የአርሶም የአርብቶ አደሮች አገር ናት፡፡አርሶ አደሮች በአብዛኛው ደጋና ወይና ደጋ በሆነው የአገሪቱ ክፍሎች ይኖራሉ፡፡
አርብቶ አደሮች ደግሞ ቆላማውን የአገሪቱን ክፍሎች ይዘው በአፋር፥ኦሮሚያ፥ሶማሌ፥ደቡብ እትዮጵያ፤ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፥ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ሕይወታቸውን ይመራሉ፡፡
የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የተረጋጋ ሕይወት የማይመራና በአመራረት ሂደት በችግሮች የተሞላ ነው፡፡
ታዲያ እነዚህ ጠረፋማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች የሚደግፉበትና ችግሮቻቸውን ለማቃለል የሚረዳ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡
የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት በአራት ምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ በመንቀሳቀስ
የአርብቶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻልና የድርቅ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው።
ፕሮጀክቱ ከ2015 አጋማሽ ጀምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ የ115 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በኢትዮጵያ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ውስጥ በሚገኙ በ187 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ ሁለት ዓበይት ምሰሶዎች ያሉት ሲሆን፥ አንደኛው በአርብቶ አደሩ አካባቢ የድርቅ አደጋ ስጋት መቀነስና አካታች የሆነ የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የእንስሳት ልማት እሴት ሰንሰለትና የግብይት ሥርዓት ማጠናከር ነው።
በእንስሳት ኢንሹራንስ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የቁም እንስሳት ማቆያ ማዕከላት ግንባታና የንግድ ተደራሽነት በማሳለጥ የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትና ዘላቂ አቅም ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አስታውቋል፡፡
ይህም በአርብቶአደር አካባቢዎች የእንስሳት ሀብቱ በድርቅ እንዳይጎዳ በማድረግ የእንስሳት ኢንሹራንስና የብድር አገልግሎት በማመቻቸት፣ የምግብ ዋስትናና የገቢ ምንጭ በማሳደግ ረገድ ጅምር ውጤቶች ተገኝተዋል።
ፕሮጀክቱ ባከናወናቸው ተግባራት የእንስሳት ኢንሹራንስ በመመዝገብና ቅድመ ክፍያ በመክፈል ፕሮጀክቱ ከጀመረበት አንስቶ ባሳለፋቸው ምዝገባ ጊዜያት ወደ 200 ሺህ አርብቶአደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ከነዚህም ከ47 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች ኢንሹራንስ ተቀብለው ለእንስሳቱ ውሃ፣ መኖና መድኃኒት በመግዛት ተጠቃሚ መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሰባት ሁሉን ያሟላ የእንስሳት ማቆያ ማዕከላት፣ የእንስሳት ሕክምናና ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ የእንስሳት ጤና ምርመራ ማዕከል እንዲሁም የኳራንታይን፣ የገበያ መሰረተ ልማት ማዕከላት ግንባታና እድሳት ተከናውነዋል፡፡
ይህም በእንስሳት ግብይት ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር በመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብሏል መረጃው።
ፕሮጀክቱ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተሻሻለ የእንስሳት ልማት፣ የኢኮኖሚ አካታችነትና ጠንካራ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ለውጥ ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ግብርና
አርብቶ አደር
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!