
ኢትዮጵያውያን ለዘመናት አትሌቶቻቸው ወደ ውጭ ልከው በታላላቅ ውደድሮች ድል ሲያደርጉ በዓይናቸው ለማየት ሳይችሉ ኖረዋል።በቀጥታ ስርጭት ወይም በዜና ይሰሙ እንደሆን እንጂ።
የታላላቅ አትሌቶች መፍለቂያና ከወርቅ በመለስ ያሉት ሜዳሊያዎች ያንሱናል ብሎ በአትሌቶቹ ብቃትና አሸናፊነት የሚኮራ፤አትሌቶቹም የወርቅ ሜዳሊያ ካላገኙ፤ሕዝባችን ያዝንብናል ብለው ይቅርታ የሚጠይቁበት አገር ሆና ኖራለች።
በዓለም ታላላቅ ደረጃ ባላቸው የኦሎምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በአትሌቲክስ ዘርፍ ውድድሮች ሠንጠረዥ ውስጥ ገብቶ ከዓለም በተወሰነ ደረጃ፤ከአፍሪካ ደግሞ ከቀዳሚዎቹ መካከል ይዘው የሚመለሱ ድንቅ አትሌቶች ያላጣች አገር ባለቤት ነች- ኢትዮጵያ።
በነዚህ ታላላቅ ውድድሮች በሳይንስና ቴክኖሎጃ ዳብረዋል፤በኢኮኖሚ ደረጃቸውም ሰፊ የገቢ ልዩነት አላቸው ከሚባሉ አገሮች በላይ ከፍ ብሎ የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያሰቅሉና ብሔራዊ መዝሙሯን የሚያዘምሩ ወንድና ሴት ቀጫጭን እግሮች በዘመናት መካከል አጥታሞ አታውቅም።
ኢትዮጵያ,በዓለም አትሌቲክስ መልክዓ ምድር ጎልታ እንድትታይ ያደረጉ የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሯጮቾ ወላድ ናት።ከ180 ያላነሱ አገሮች በታላላቆቹ ውድድሮች ተሳትፈው አንድ የነሐስ ሜዳሊያ እንኳን አጥተው ወደ አገሮቻቸው የሚመለሱት ብዙዎቹ መሆናቸውን የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች አያጡትም።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶችቻቸው ውድድር ካላቸው ቀንና ሰዓቱን ለይተው በመያዝ እንቅልፋቸው አጥተውመ ቢሆን ቀደም ሲል በቴሌቪዥን ዛሬ ደግሞ ውድድሮቹ ይተላለፉባቸዋል በሚባሉ የማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን(ሶሻል ሚዲያ)መከታተል የኖረ ባህላቸው ነው።
አትሌቶቹ ውቅያኖሶችንና ባህሮችን አቋርጠው ከዓለም ምርጥ አትሌቶች ተወዳድረው ሲያሸንፉ ለማየት ያልታደለው ኢትዮጵያዊ ተከትሏቸው ለመሄድ የአቅም ጉዳይ ይይዘዋል። በአውሮፓ፣አሜሪካና እስያ አህጉሮቸ የሚካሄዱ ውድድሮችን በአካል ለማየት አይችልም።
በሌላ በኩል ዓለም በአካል አይቷቸውና አድናቆቱንም የሚገልጽላቸውን በችሎታቸውና በብቃታቸው የሚያደንቃቸውን ምርጥ አትሌቶች በዓይኑ ለማየት ቢፈልግም ሳይችል ኖሯል።
ጊዜው ፈቀደና ዘንድሮ አፍሪካም የታላላቅ አትሌቶች መፍለቂያ ብቻ ሳትሆን፤ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የምድሪቱ ታዋቂ አትሌቶች የሚወዳደሩባት አህጉር የሚያደርጋት ውድድር እንድታጋጅ ዕድሉን ተሰጣት።
የዓለምን አትሌቲክስ ውድድሮችን በበላይነትና የሚመራው የዓለም አትሌቲክስ ተቋም ግራንድ ፕሪ ብሎ በሚጠራው የአንድ ቀን ወድድር ከአህጉሪቱ አራት አገሮች መርጦ ውድድሮችን ዛሬ አንድ ብሎ በአዳስ አበባ ጀመረ።
በቀጣይ ወደ ኬንያ፣ቦትስዋናና ደቡብ አፍሪካ ውድድሮችን ለመቀጠል።
ተቋሙ በየአገሮቹ ለሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ደረጃ ይሰጣል፦የወርቅ፣የብር፣የነሐስና ቻሌንጀር በሚል።ለአዲስ አበባ የተሰጣትና ያስተናደችው ውድድር የነሐሰ ደረጃ ተብሎ ነበር።የውጤታማ አትሌቶችን አገር የማይመጥን፤ጅምር በመሆኑ ግን የሚቀበሉት።
ታዲያ ኩሩውና ድንቁ አትሌቲክስ ወዳድ ሕዝብ ባሳየው ድጋፍና ፍቅር፣በውድድሩ አዘገጃጀት ብቃትና መንግሥት ለውድድሩና ለሰፖርቱ ያለውን ድጋፍ ተመልክቶ ተቋሙ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ አንድ ግራንድ ብቻ በቃው።
አዲስ አበባ ከዓለም 10 የወርቅ ደረጃ ያለው ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን ውድድርን ከሚቀጥለው ዓመት ጁምሮ እንድታካሂድ ተወስኖላታል።
አዲስ አበባ እንደ ኒው ዮርክ፣ሜልቦርንና ናይሮቢ በመሰሉ ከተሞች ተርታ ተመድባ ውድድሩን በከፍታና በርካታ አገሮችን በሚያሳትፍ መልኩ ማስተናገድ ትጀምራለች።
የዓለም ታላላቅ አትሌቶችን በአገሩ ሲወዳደሩ ያየው ተመልካችም ለብቃታቸው አድናቆቱን፣በኢትዮጵያ መጥተው በመወዳደራቸው ደግሞ ደስታውን ሲገልጽላቸው ነበር።
ኢትዮጵያም በሚመጥናት ደረጃ ከቀጣዩ ዓመት ጀምራ ውድድሩን እንድታዘጋጅ መወሰኑም እንዳሰደሰተው ሲገልጽ አምሽቷል።
የዓለም አትሌቲክስ ተቋም የሚያሰናዳቸው አህጉራዊ ግራንድ ፕሪ ውድድሮች በአራት ደረጃዎች ይከፈላሉ። ለነዚህ ውድድሮች ደረጃ የሚወሰነው በሽልማት መጠን፣ በውድድሩ ጥራትና በሚያስገኙት የደረጃ ነጥብ ላይ ተመስርቶ ነው።
ከነዚህም በወርቅ ደረጃ የሚሰናዳው ከዳይመንድ ሊግ ቀጥሎ ከፍተኛው የአንድ ቀን ውድድር ደረጃ ነው።ቀሪዎቹ በብር፣በነሐስና ቻሌንጀር ተብለው የተመደቡ ናቸው።
ከነዚህም በወርቅ ደረጃ የሚሰናዳው ከዳይመንድ ሊግ ቀጥሎ ከፍተኛው የአንድ ቀን ውድድር ደረጃ ነው።ቀሪዎቹ ብር፣ነሐስና ቻሌንጀር ተብለው የተመደቡ ናቸው።
በወርቅ ደረጃ የሚካሄደው ውድድር አጠቃላይ የሽልማት ገንዘብ ቢያንስ 200ሺህ ዶላር ሽልማት ሊኖረው ይገባል።
ለተወዳዳሪዎቹ ከፍተኛ ነጥብ ያስገኛል።ቢያንስ ሦስት ተወዳዳሪ አትሌቶች ከዓለም 50 ምርጥ ደረጃ ውስጥ መገኘት አለባቸው።
የየአህጉሩ አትሌቲክስ ማህበራት የሚመሩትና ቢያንስ 75ሺህ ዶላር የሚያሸልም ውድድር ደግሞ የብር ደረጃ የተሰጠው ነው ።
በእያንዳንዱ ውድድር ቢያንስ አምስት ሺህ ዶላር ሽልማት ሊኖረው የሚገባው ይህ ውድድር፣ የምድብ "ቢ" ነጥብ ያስገኛል።
በውድድሩ ከዓለም 100 ምርጥ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ቢያንስ ሦስት አትሌቶች መሳተፍ አለባቸው።
ለታዳጊ አትሌቶችና ለአዳዲስ አዘጋጅ አገሮች ዕድል የሚሰጠው የነሐስ ደረጃ የተሰጠው ውድድር መሆኑንም መረጃው ያሳያል።
ለውድድሩ የሚመደበው አጠቃላይ ሽልማት ቢያንስ 25ሺህ ዶላር ይመድበለታል። ውድድሩ"ሲ" ነጥብ ያሰጣል።ቢያንሰ ከሦስት አገሮች የተውጣጡ ስድስት አትሌቶች መወዳደር አለባቸው።
ቻሌንጀር የተባለው አራተኛውና የመግቢያ ደረጃ ያለውና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 የተጀመረ ውድድር ነው።
በዚህ ውድድር ለሚካፈሉ የሚሰጠው በአጠቃላይ ከ20ሺህ ዶላር ያላነሰ ሽልማት ይሰጣል።
የውድድሩ ዓላማ አነስተኛ አቅም ላላቸው አዘጋጆችና በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች ዓለም አቀፍ ልምድ የሚገበዩበት መሆኑን መረጃው ያሳያል።
የዓለም አትሌቲክስ በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት 11 የወርቅ ደረጃ ያላቸወን ውድድሮች በማካሄድ ላይ ነው፡፡ከነዚህም በሜልቦርን፣ አውስትራሊያ የተዘጋጀው ባለፈው ወር ተከናውኗል፡፡ቀጣዩ ውድድር በያዝነው ወር ናይሮቢ፣ ኬንያ ይካሄዳል።
ጃፓን፣አሜሪካና የአውሮፓ አገሮች ደግሞ 10 ውድድሮችን ከግንቦት እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ እንደሚያካሂዱ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያስረዳል፡፡
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!