እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:10:17 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የአፍሪካ መሠረተ ልማት ችግሮች፣ጅምሮችና ቀጣይ ተግባራት

3 ደቂቃ ንባብ
የአፍሪካ መሠረተ ልማት ችግሮች፣ጅምሮችና ቀጣይ ተግባራት
ፕሮጀክቶቹ ለሕዝቡ አቅም ይፈጥራሉ።አርሶ አደሮችን ከገበያዎች፣ነጋዴዎችን ከደንበኞች፣ተማሪዎችን ከትምህርት በማገናኘት-አቅምን ከሕልሞች አገናኝቶ ሕይወትን ይቀይራሉ።

መሠረተ ልማት ጨዋታ ቀያሪ ነው በኢኮኖሚው ላይ ትክክለኛ ልዩነት ማምጣት ይችላል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡አፍሪካ ግን የሚያስፈልጓትን የመሠረተ ልማት ተቋማት አልገነባችም፡፡

የአህጉሪቱ መሠረተ ልማት ጉድለቶች የኢኮኖሚ ዕድገቱን በየዓመቱ ሁለት በመቶ፤ምርታማነትን በ40 በመቶ ይቀንሱታል፤የኤሌክትሪክ አቅርቦት 65ከመቶ አፍሪካውያን አገልግሎቱን አያገኙም የሚለን የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰነድ ነው፡፡

የውሃና ንጽህና አገልግሎት በአብዛኛዎቹ አገሮች በዓመት ከአንድ በመቶ በታች የሚመደብለት ዘርፍ በመሆኑ በአግባቡ አለመልማቱን ይገልጻል፡፡

ባንኩ የመኖሪያ ቤቶች እጥረት-ብዙ አፍሪካውያን የተመቸ ለኑሮ በተመቸ ቤት አይኖሩም  ይላል፡፡

በትራንስፖርት-በዘርፉ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ሰብዓዊና ማህበራዊ ሀብቱ ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ያለመሥራታቸውን ያመለክታል››

በመንገድ  ዘርፍ  በተከናወኑ ሥራዎች ተጠቃሚ  የሆነው ከሕዝቡ ገሚሱ ሲሆን፣ገሚሱ ተደራሽ አልሆነም፡፡በአህጉሪቱ ከ60ሺህ ኪሎ ሜትር መንገዶች ደረጃውን ማሻሻል አለበት፡፡

የአህጉሪቱ አየር ትራንስፖርት በዝቅተኛ ደረጃ  የለማና የደህንነት ስጋት ያለበት መሆኑን ገልጾ፣ያሏት 64ወደቦች  በዝቅተኛ ደረጃ  የለሙ መሆናቸውን ሰነዱ ያሳያል፡፡

የባቡር መሥመሮች 84ሺህ ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያላቸው መሥመሮች  ቢዘረጉም፣ነገር ግን በአብዛኛው ኋላ ቀር የዕድገት ደረጃ  የሚገኙና  መዘመንና መስፋፋት  ይቀራቸዋል ይላል፡፡

ባንኩ  የአፍሪካ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በጣም በዝቅተኛ  ደረጃ ላይ ነው በማለትም ይገልጸዋል፡፡

ችግሮቹን ለማቃለል የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንየአፍሪካ መሠረተ ልማት ልማት ፕሮግራም(Program on Infrastructure Development Africa- PIDA )ዘርግቷል፡፡አፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት(ኔፓድ) የአፍሪካ ልማት ባንከ የሚያሳትፍ መሠረተ ልማት ላይ የሚሰራ አህጉራዊ መርሐ ግብር ነው።

መርሐ ግብሩ በአራት ዋነኛ ዘርፎች ይሰራል።እነርሱም፦ኢነርጂ፣ትራንስፖርት፣ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂና ድንበር ተሻጋሪ ውሃ ላይ ሲሆን፣ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ልማት ማፋጠንና የተቀናጀ ዘመናዊ መሠረተ ልማት መገንባት ነው፡፡

ግቡ አህጉራዊ ትስስርን  ማጠናከር ባነሰ፣የአፍሪካን እርስበርሰ ንግድ ልውውጥን ማሳደግና ለአፍሪካ ንግድ እንቅስቃሴ አስተዋጽዖ ማድረግ የሆነው መርሐ ግብር፣ቀጣናዊ ትስስር ፥ድንበር  ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት በማካሄድ የኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር ይሰራል ይላል ሰነዱ።

በመርሐ ግብሩ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ከዕቅድ እስከ አፈጻጸም ክትትል ይደረግባቸዋል፤ፕሮጀክቶቹ አስተማማኝና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙና ብሎም ለአህጉሪቱ የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚያገለግሉ እንዲሆኑም ደደረጋል።

በአህጉሪቱ በመሠረተ ልማት የለሙት የደቡብና የሰሜን አፍሪካ ቀጣና የሚገኙ አገሮች በተቀሩት ቀጣናዎች የሚገነቡት ፕሮጀክቶች ባለባቸው የተወሰኑት ባለባቸው የፋይናንስ እጥረት፣የተወሰኑት ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና ጥገና የሚያሰፈልጋቸወ በመኖራቸው ዕድገታቸው መጓተት ገጥሞታል።

መርሐ ግብሩ ንግድን ያመቻቻል፤ግንኙነትን ያቀላጥፋል፤አካታች ዕድገትን ያፋጥናል በማለትም ያመለክታል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ለሕዝቡ አቅም ይፈጥራሉ።አርሶ አደሮችን ከገበያዎች፣ነጋዴዎችን ከደንበኞች፣ተማሪዎችን ከትምህርት በማገናኘት-አቅምን ከሕልሞች አገናኝቶ ሕይወትን ይቀይራሉ በማለትም ያብራራል፡፡

መርሐ ግብሩ 69 ፕሮጀክቶችን በኢነርጂ፣በውሃና ትራንስፖርት ዘርፎች ያካሂዳል።ከፕሮጀክቶቹ 90በመቶ ያህሉ በመንግሥታት የሚካሄዱ ሲሆን፣የግል ዘርፍ ተሳትፎ ያደርግባቸዋል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በአፍሪካ መሠረተ ልማት መርሐግብር የታቀዱ 69ፕሮጀክቶችን 160ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ያሰፈልጋል ይላል ከአምስት ዓመታት በፊት ያደረገው ጥናት፡፡

የላሙ ወደብ-ደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ ትራንስፖርት( LAPSSET)ኮሪደር ልማት የኬንያን፣ኢትዮጵያንና ደቡብ ሱዳንን ግንኙነት በማሳለጥ፣የንግድ ወጪን በመቀነስና ኢኮኖሚያዊ ውህደት በማቀላጠፍ ሚናው የላቀ መሆኑን አስረድቷል፡፡

የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ሌላው የአፍሪካን መሠረተ ልማት ሁኔታ ያጠና ተቋም ነው፡፡ተቋሙአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና ሽግግር ለማምጣት በየዓመቱ በአማካይ 155ቢሊዮን ዶላር በጀት መመደብ አለባት።

በዚህም የመሠረተ ልማት ተቋማትን ለማዘመንና የአህጉሪቱን የአገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት(GDP)በእጥፍ ለማሳደግ ይረዳል።

ይህም በአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ተቀረፀውን አጀንዳ 2063 ግብ በሰባት በመቶ የሚልቅ የአገር ውስጥ አጠቃላይ ዕድገት ለማስመዝገብ ያስችላታል ብሏል።

ተቋሙ ለዚህም  ይረዳሉ  ያላቸውን መፍትሔዎች  ያመላከተ ሲሆን፣ለመንገድ፣ለባቡር መሥመሮች፣ለፋይበር አፕቲክስና ለሶላር ኢነርጂ  ልማት ትኩረት እንዲሰጥ አመላክቷል፡፡

ስትራቴጂያዊ ለሆኑ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ሰጥቶ ማልማትበዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ክህሎትንና አቅምን በመንግሥትና አልሚዎች ማሻሻል ተገቢ መሆኑን ያሳያል፡፡

የአህጉሪቱን የመሠረተ ልማት ይዞታ ለመቀየር የአገሮችን የብድር ሁኔታ ማሻሻል፣ሥራዎችን ወጪ ቆጣቢና አሳታፊ በሆነ መልኩ ማካሄድና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መሠረተ ልማት በመቀየስ ማህበረሰቦችን ከሚገጥማቸው ጉዳት መጠበቅ ይገባል በማለትም ምክረ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡

 

 

 

 

ኢኮኖሚአፍሪካ መሠረተ ልማት

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!