እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:24 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

የኢትዮጵያ 79 ደረጃዎች ጸደቁ

2 ደቂቃ ንባብ
የኢትዮጵያ 79 ደረጃዎች ጸደቁ
ከፀደቁት ደረጃዎች መካከል አስገዳጅ የህጻናት ምግብ ደረጃዎች፣ የተከለሱ የህጻናት ምግብ መፈተሻዎች፣ አስገዳጅ የማርና ማር ውጤቶች ደረጃዎች፣ የማርና የማር ውጤት መፈተሻዎች ይገኙበታል።
1 / 2

የኢትዮጵያ 79 አዳዲስና የተከለሱ  መጽደቃቸውን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የደረጃዎች ቦርድ ካጸደቃቸው ደረጃዎች መካከል 56 አዳዲስ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ የተከለሱ ናቸው።

ቦርዱ ደረጃዎችን ያጸደቀው በምግብና ግብርና ዘርፍ፣ በመሠረታዊና አጠቃላይ ዘርፍ እንዲሁም በኤሌክትሮ መካኒካል ዘርፍ መሆኑን አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ(ዶ/ር)እንደገለጹት ከፀደቁት ደረጃዎች መካከል አስገዳጅ የህጻናት ምግብ ደረጃዎች፣ የተከለሱ የህጻናት ምግብ መፈተሻዎች፣ አስገዳጅ የማርና ማር ውጤቶች ደረጃዎች፣ የማርና የማር ውጤት መፈተሻዎች ይገኙበታል።

በተጨማሪም የሳይበር ደህንነት አስገዳጅ ደረጃዎች ከፀደቁት መካከል እንዳሉበት ተናግረዋል።

የደረጃዎቹ መጽደቅ የህጻናት ወተትን ጨምሮ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ጥራትና ደህንነትን በተገቢው መልኩ ለመፈተሽ፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራትና ተወዳዳሪነት ያሳድጋል ብለዋል።

በአገር ደረጃ ከ12ሺህ በላይ ደረጃዎች ያስረዱት ዋና ዳይሬከተ፣የጸደቁት ደረጃዎች ሥራ ላይ መዋል የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ሀብቴ በበኩላቸው፤ በቦርዱ ከጸደቁት 79 ደረጃዎች ውስጥ 28ቱ አስገዳጅ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በምግብና ግብርና ዘርፍ ስድስት የተከለሱ አስገዳጅ የግብርና ማዳበሪያ ደረጃዎች፣ ሁለት አስገዳጅ የህጻናት ምግብ ደረጃዎች፣ ሰባት የተከለሱ የህጻናት ምግብ መፈተሻዎች፣ አንድ የማርና ማር ውጤት ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ፣ ሁለት አዲስ የማርና ማር ውጤት መፈተሻዎች ከጸደቁት መካከል እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በተመሳሳይም ሁለት አዲስ አጠቃላይ የምግብ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃዎች፣ ሦስት አዲስና ዘጠኝ የተከለሱ በድምሩ 12 መፈተሻዎች መጽደቃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

በመሠረታዊና አጠቃላይ ዘርፍ ደግሞ ሦስት ጂኦግራፊያዊ መረጃ አስገዳጅ ደረጃዎች፣ አምስት አዲስ የሳይበር ደህንነት አስገዳጅ ደረጃዎች፣ 30 አዲስ የሳይበር ደህንነት መፈተሻዎች፣ ሁለት አዲስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት አስገዳጅ ደረጃዎች በቦርዱ መጽደቃቸውን ተናግረዋል።

በኤሌክትሮ መካኒካል ዘርፍ ደግሞ ስድስት አዲስ የትራንስፖርት አስገዳጅ ደረጃዎችና አንድ አዲስ የባቡር መንገድ የምህንድስና አስገዳጅ ደረጃዎች እንደሚገኙበትም አስረድተዋል።




የጥራት ደረጃዎችሳይንስና ቴክኖሎጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!