እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:10:16 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ስትራቴጂ በኬንያው ሚዲያ ዕይታ

3 ደቂቃ ንባብ
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ስትራቴጂ በኬንያው ሚዲያ ዕይታ
አሁን ኢትዮጵያ የምትሻው ለስብሰባዎቹ የሚመጡትን ተሳታፊዎች ብዛት ከመቁጠር ባለፈ፤ገንዘብ የሚያስገኝ ሀብት ማፍሪያ ማድረግን ነው።በአጭሩ የቱሪዝም ገቢ ማስገኛ አድርጎ ተጠቃሚ መሆን ነው።
1 / 2

https://www.dawan.africa/news/ethiopia-rebuilds-tourism-with-urban-renewal-and-heritage-strategy 

ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ቱሪዝም ዘርፍ የምትመለስበትን ሰፊ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እያዘጋጀች ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያሰናዱት አዲሱ ስትራቴጂ አገሪቱን ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ያደርጋታል።ስትራቴጂው የከተማ ተሃድሶ(መልሶ ግንባታ)፣የቅርሶች እድሳትና አገልገሎት አሰጣጥ ማሻሻልን ያካትታል።

የነዚህ ተግባራት ቅንጅት የሚያሳየው ደግሞ ታላቁን ምስል ተመልሶ ይከስተዋል ይላል መሠረቱን ኬንያ ያደረገው "ዳዋን አፍሪካ" ኦንላይን ሚዲያ በቤኔዴታ ምዋራ የሰፈረው ጽሁፍ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስትራቴጂው የተዘጋጀው  የኢትዮጵያን "አዲሱን ገጽታ" ለዓለም ለማሳየት ነው።ዓለም በአገሪቱ ላይ ያለውን ዕይታ በአዲስ መልክ ማስተዋወቅ ነው በማለት ያብራራል።

አዲሱ ገጽታ የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ አሴቶች አጉልቶ የሚያሳይ ይሆናል ሲልም ያክላል።

በዘርፉ በሚደረገው ሽግግር ዋነኛ ትኩረት የተሰጣት አዲስ አበባ ናት፡፡በከተማዋ የሚካሄደው የወንዞች ዳርቻ ፕሮጀክት የመዲናዋን መልክዓ ምድር የሚቀይር ታላቅ ሥራዎች አንዱ ሲሆን፥50ኪሎ ሜትር ርዝመት ይሸፍናል፡፡

በፕሮጀክቱ የተካተቱ ስምንት ወንዞች ውስጥ የተበከሉትንና ለጤና አደገኛ የተባሉትን አካባቢዎች ወደ አረንጓዴነት፣የሕዝብ መዝናኛ ፓርክነትና ሌሎች ዓይነት መዝናኛዎች ለመለወጥ ያስችላል።

ባለሥልጣናቱ እንደሚሉት በከተማዋ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ሥነ ውበትን የማምጣት ሳይሆን፤አካባቢያዊና ማህበራዊ እሴቶችን መመለስ ነው።የተበከሉ የውሃ ማመንጫዎች በዘመናዊ መንገድ ታክመዋል።ቆሻሻ ወደ ግብርና ግብዓትነት እየተቀየረ ነው።

የእግረኛ መንገዶች፣የቢስክሌት መንጃዎችና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ነዋሪዎች ከከተማዋ ጋር ያላቸውን መስተጋብር በመቀየር አኗኗራቸውን ከቱሪስቶች ፍላጎት ጋር እየተቃኘ ነው።

በኢትዮጵያ የወንዞች ዳርቻ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ማሳያ የሆነ ይመስላል።ለአብነትም ሐዋሳ፣ቢሾፍቱና ባህር ዳር ራሳቸውን መልከው የሚያድሱባቸው ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በማካሄድ ላይ ናቸው።

አሁን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሞዴል ተቀይሯል።በታሪካዊ ቅርሶች ላይ ጥገኛ የነበረው አካሄድ ተለውጦ በተቀናጀ መንገድ የሚከናወን ተፈጥሮ፣መሠረተ ልማትንና ከተሜነትን ያካተተ ሞዴል ሆኗል ብሏል ዘገባው።

በአገሪቱ ቱሪዝምን የማስፋፋትና የማጠናከር ሂደት ዘመናዊ ቱሪዝም ከሚሻው ባህልና ዝመናን ባዋሃደ መልኩ መዳረሻዎችን ከመጎበኘት ጋር ተሰናሰኗል።

ኢትዮጵያ በታሪካዊና ባህላዊ እሴቶቿ የነበራትን ዕውቅና በአሁኑ ወቅት የመሠረተ ልማት ተቋማትን ደረጃ አሳድጋ ጎብኚዎችን ለመሳብ አዲሱን ገጽታዋን እያስተዋወቀች ናት።

አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ እንደመሆኗ፤በየዓመቱ የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን ታስተናግዳለች።ይህም የዓለም ትኩረት ማዕከል ሆና ለመቆየት አስችሏታል።

አሁን ኢትዮጵያ የምትሻው ለስብሰባዎቹ የሚመጡትን ተሳታፊዎች ብዛት ከመቁጠር ባለፈ፤ገንዘብ የሚያስገኝ ሀብት ማፍሪያ ማድረግን ነው።በአጭሩ የቱሪዝም ገቢ ማስገኛ አድርጎ ተጠቃሚ መሆን ነው።

ከዚህ በላይና ባሻገር መንግሥት ቁልፍ ለሆኑ የቅርስና የቱሪዝም ማዕከላት ትኩረት ሰጥቷል።በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ)ዕውቅና ያገኘው የጎንደር ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትን አድሷል።ዘመናዊ የመስተንግዶ መሠረተ ልማትን በመዘርጋት የጎብኚዎችን ቁጥር ከሚያሳድጉ ተግባራት ጋር ማቀናጀትን አየተተገበረ ነው።

የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች ባለብዙ ዘርፍ እንዲሆኑም በመደረግ ላይ ይገኛል።የመገጭ መስኖ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ታክሎበት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ መስህቦች ውስጥ የሚካተት መዝናኛ እንዲሆን ለማድረግ ታቅዷል።ይህም ይሄኛው የአገሪቱ ክፍል ከታሪካዊ ቅርሶች ያለፈ ሌላ መስህብ እንዲኖረው ያደርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይላል ይኸው ኬንያን መቀመጫው  ያደረገው ሚዲያ፣ባሌ አካባቢ ያሉትን የቱሪስት መስህቦች ምቹና ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመሳብ በመሰራት ላይ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች ቁጥርና ደረጃ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፤የአገልግሎት አቅርቦት ችግር ተወዳዳሪነቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ባለሥልጣናት ያምናሉ።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ዜጎችና አገልግሎት አቅራቢዎች እንግዶችን የሚያስተናግዱበት  መንገድ መቀየር እንዳለበት መጠየቃቸውን በማስታወስ።መስተንግዶ በባለሙያነት፣በጥሩ ፈገግታና በመከባበር ላይ ተመሥርቶ መሰጠት እንዳለበት አመላክተዋል።ቱሪዝም በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሆነ ሊጤን ይገባዋል ሲልም ጽፏል።

ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለችው የቱሪዝም ስትራቴጂ አገሪቱ በዓለም የቱሪዝም ገበያ ተወዳዳሪና ተገቢ ሥፍራዋን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት አካል ነው።አካበቢን በመጠበቅና በመነሰከባከብ፣በመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ በሚደረግ ኢንቨስትመንትና በቅርሶች እድሳት ቱሪስቶችን ለመሳብ የሚያሰችላትን አካሄድ መርጣለች።ይህም ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ቱሪስቶችን ለመሳብ ያስችላታል።

ፈተናው የአፈፃፀም ነው።ጅምሩን በጋለ መንፈስ ማስቀጠል፣የአገልግሎት ጥራትን ማረጋገጥና የመሠረተ ልማት ተቋማትን ማስጠበቅ ላይ።አነዚህን ተግባራት ማድረግ ከተቻለ፤የአገሪቱን የረጅም ጊዜ ሕልምን ወደ ረጅም ጊዜ ዕድገት ይቀየራል።

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የያዘችው ዕቅድ ከተሳካ በዘርፉ የሚገባትን ሥፍራ ማግኘት  ብቻ ሳይሆን፤ለሌሎች አፍሪካ አገሮች ምሳሌ ያደርጋታል።

ባህልን፣ተፈጥሮንና ከተሜነትን አቀናጅቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠቀስ የቱሪዝም መስህብ ሆና ሲል ሚዲያው ጸሁፉን አብቅቷል።






ኢኮኖሚመገናኛ ብዙኃንቱሪዝምየቱሪዝም ስትራቴጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!