እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:48 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀ

1 ደቂቃ ንባብ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀ
1 / 3
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀ።
  
ሻምፒዮናው ከመጋቢት 15 -20/2018 በአዲስ አበባ አደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ተካሂዷል።

በሻምፒዮናው ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን (Time Tronics) ሥራ ላይ ውሏል።

ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ታልሞ ሻምፒዮናው መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ሻምፒዮናውን 36 ክለቦች፣ ተቋማት፣ ዘጠኝ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮችን የወከሉ  ከአንድ ሺህ በሚበልጡ ተወዳዳሪዎች ተካፍለውበታል።

ከተወዳዳሪዎቹ 621 ወንዶች ሲሆኑ፤ 436ቱ ደግሞ ሴቶች ነበሩ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል ቀዳሚ በሆነው ሻምፒዮና ማጠቃለያ 10 የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውንበታል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮናውን በበላይነት ያጠናቀቀበትን ውጤት አስመዝግቧል።

መቻል ሁለተኛ ሲወጣ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህንና የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ለአሸናፊ ክለቦችና አትሌቶች የገንዘብ፣ ዋንጫዎችንና ሜዳሊያዎችን ሰጥተዋል።

ለሻምፒዮናው  10 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉም በመዝጊያው ሥነ ሥርዓት ላይ ተነግሯል።



ስፖርትየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናአትሌቲክስ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!