
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ የጥራት ደረጃዎችን መርምሮ ዛሬ አፀደቀ፡፡
ቦርዱ ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባ ያፀደቃቸው የንግድ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጡ፣ የገበያ ሥርዓቱን የሚያዘምኑና ለኢኮኖሚ ዕድገት ፋይዳ ያላቸው ቁልፍ ብሔራዊ አስገዳጅ ደረጃዎች ናቸው።
የጸደቁት ደረጃዎች በዋናነት በምግብና እርሻ፣ በኢንዱስትሪ፣ በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በሳይበር ደህንነት፣ በጂዖግራፊያዊ መረጃ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የቦርዱ ሰብሳቢና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ እንደገለጹት፤ የጸደቁት ደረጃዎች ለአገሪቱ የጥራት መሠረተ ልማት ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው።
ይህም አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ብለዋል።
ተቆጣጣሪ ተቋማትም ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ለአገር ዕድገት መሠረት መሆኑን በመገንዘብ የጸደቁት ደረጃዎች ወጥነት ባለው መልኩ ወደ ተግባር እንዲገቡ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለደረጃዎቹ ተፈጻሚነት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!