እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:18 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

የኳንተም ኮምፒዩተሮች የምስጠራ ሥርዓቶች እንዳይሰብሩ ጥንቃቄ ይደረግ-ጎግል

2 ደቂቃ ንባብ
የኳንተም ኮምፒዩተሮች የምስጠራ ሥርዓቶች እንዳይሰብሩ ጥንቃቄ ይደረግ-ጎግል
የኳንተም ቴክኖሎጂ በሳይንስና ሕክምና ዘርፍ ትልቅ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የዲጂታል ደህንነት ስጋቱ ግን ከወዲሁ መላ ካልተፈለገለት የዓለማችንን የመረጃ ፍሰት ምስቅልቅል ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ባለሙያዎች ስጋታቸውን ከወዲሁ በመስጠት ላይ ናቸው።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል (Google)፤ የኳንተም ኮምፒዩተሮች በአሁኑ ወቅት የምንጠቀምባቸውን የዲጂታል መረጃ መከላከያ ምስጠራዎች (Encryption) ሰብረው እንዳይገቡ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ።

የኳንተም ኮምፒዩተሮች ምስጠራዎቹን ሰብረው የመግባት አቅም የሚኖራቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2029 ሊሆን እንደሚችልም አመላክቷል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ድረስ ሊከሰት ይችላል የተባለው አደጋ አስቀድሞ እየመጣ በመሆኑ ከአሁኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኩባንያው አስገንዝቧል። 

ቀደም ሲል "Q-Day" ተብሎ የሚጠራውና የኳንተም ኮምፒዩተሮች አሁን ያሉትን የሳይበር ደህንነት መከላከያዎች ዋጋ ቢስ የሚያደርጉበት ወቅት ይዘገያል ተብሎ ቢታሰብም፣ ግን የቴክኖሎጂው እድገት ፈጣን እየተቃረበ መምጣቱን ገልጿል። 

ኩባንያው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ የኳንተም ኮምፒዩቲንግ ዘርፍ በሃርድዌርና በስሌት አቅም እያሳየ ያለው ከፍተኛ መሻሻል፣ በተለይም የባንክ፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት የሚጠቀሙባቸውን የዲጂታል ፊርማዎችና የመረጃ ምስጠራዎች ለአደጋ የሚያጋልጥ ሆኗል። 

በተለይም አሁን ሰርቆ ቆይቶ መፍታት (Store-now-decrypt-later) የተባለው የጥቃት ስልት አሳሳቢ መሆኑ ተጠቁሟል። 

ይህም ማለት የሳይበር ወንጀለኞች በአሁኑ ወቅት የተመሰጠሩ መረጃዎችን ሰርቀው በማከማቸት፣ የኳንተም ቴክኖሎጂው ዝግጁ ሲሆን ወደፊት የተመሰጠሩ መረጃዎችን ለመስበር እቅድ መያዛቸውን ያሳያል ብሏል ኩባንያው። 

ይህንን ስጋት ለመመከት ጎግል መጪው የ"አንድሮይድ 17" (Android 17) ኦፕሬቲንግ ሲስተም አዲሱን የኳንተም መቋቋሚያ ቴክኖሎጂ (PQC) አካቶ እንዲወጣ ማድረጉን አስታውቋል። ይህም በተለይ ለዲጂታል ፊርማዎች ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚሰጥ በማመላከት። 

እንደ ብሪታንያው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል (NCSC)ና የአሜሪካው ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ (NSA) ያሉ ተቋማት ለሽግግሩ እስከ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2033 እና 2035 ድረስ ሊቆይ ይችላል የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጡም፣ የጎግል አዲሱ ማስጠንቀቂያ ግን የዓለም የቴክኖሎጂ ተቋማት አሁኑኑ ዝግጅት እንዲጀምሩ የሚያስገድድ ሆኗል። 

የኳንተም ቴክኖሎጂ በሳይንስና ሕክምና ዘርፍ ትልቅ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የዲጂታል ደህንነት ስጋቱ ግን ከወዲሁ መላ ካልተፈለገለት የዓለማችንን የመረጃ ፍሰት ምስቅልቅል ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ባለሙያዎች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።


ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂሳይንስና ቴክኖሎጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!