እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:01 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:01 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
የይለፍ ቃላት ዘመን እያበቃለት ይሆን?
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
የዘርፉ ባለሙያዎችም ተቋማት በባዮ ሜትሪክስ (የጣት አሻራ እና የፊት ገጽታ) ላይ ወደሚሰሩ "ፓስኪዎች" (Passkeys) እንዲሸጋገሩ መክረዋል፡፡
የይለፍ ቃላት (Passwords) ዘመን እያበቃለት ይሆን?በማለት ጽሁፉን በጥያቄ ይጀምራል፡፡
አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የሳይበር ጥቃቶች የሚጀምሩት በተሰረቁ የተጠቃሚ መለያዎች መሆኑን ተከትሎ፣ የይለፍ ቃላት (Passwords) ለከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ሆነዋል ይለናል የመረጃችን ምንጭ።
በቅርቡ የወጡ የደህንነት ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ተጋላጭነቱ እየሰፋ በመምጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች "የይለፍ ቃል አስተማማኝነቱ እያበቃ ነው" የሚል ማስጠንቀቂያ በመስጠት ላይ ናቸው።
የመረጃ መንታፊዎች ሰራተኞችን ለማታለል እውነተኛ የሚመስሉ የሐሰት መግቢያ ገጾችን በመጠቀም መረጃዎችን እየሰረቁ መሆናቸው ተነግሯል ይለናል በመለጠቅም፡፡
በዚህም የተጠቃሚን መዘናጋት በመጠቀም የብዙ-ደረጃ ማረጋገጫን (MFA) በመጥለፍ ወደ ተቋማት ምስጢራዊ መረጃ ሰርገዉ መግባት መቻላቸው የችግሩን አሳሳቢነት ጨምሮታል።
በተለይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሳይበር ወንጀለኞች የሚልኳቸውን መልዕክቶች ይበልጥ አሳማኝ እንዲሆኑና ሰዎችን በቀላሉ እንዲያታልሉ እገዛ እያደረገላቸው መሆኑን አመላክቷል።
የይለፍ ቃላት የተፈጠሩት ሠራተኞች በቢሮ ውስጥ ብቻ በሚሰሩበት ዘመን እንደነበር ያስታወሰው ጥናቱ፣ አሁን ግን ሥራ በየትኛውም ቦታና በግል መሣሪያዎች ጭምር የሚከናወን በመሆኑ የቆዩት የደህንነት ፖሊሲዎች በቂ አለመሆናቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያስረዳል።
የቲም ቪወር (TeamViewer) የ2025 ጥናት እንደሚያሳየው፣ 80 በመቶ የሚሆኑ ሠራተኞች ከመግቢያ መረጃ ጋር የተያያዘ ችግር ገጥሟቸዋል፡፡
ውስብስብ የይለፍ ቃል ሕጎችም ተጠቃሚዎች መረጃቸውን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ እንዲያስቀምጡ እያገፋፏቸው መሆኑ ተጠቅሷል።
የዘርፉ ባለሙያዎችም ተቋማት በባዮ ሜትሪክስ (የጣት አሻራ እና የፊት ገጽታ) ላይ ወደሚሰሩ "ፓስኪዎች" (Passkeys) እንዲሸጋገሩ መክረዋል፡፡
ይህም የመረጃ መንታፊዎች መረጃን ቢሰርቁ እንኳን ያለ ተጠቃሚው መሣሪያ መጠቀም ስለማይችሉ ጥቃቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰው ጠቁመዋል።
የይለፍ ቃላት መጠቀም በእርግጥም
እያበቃ ይመስላልና አማራጮችን ማማተር የግድ እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡
ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የይለፍ ቃላት
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!