እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

1 ደቂቃ ንባብ
ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
ኦፕሬሽኖቹ በመኪና መለዋወጫ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግንባታ ግብዓቶች፣ በሥጋ ቤቶች፣ በአልባሳት እንዲሁም በወለል ምንጣፍ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ መካሄዳቸውን አመልክቷል፡፡

ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ 55 ግብር ከፋዮች ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ከስድስት ወራት የሚደርስ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነባቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እንዳስረዳው ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት በማስፈን ለከተማዋ ልማት የሚውል ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ያለደረሰኝ ሽያጭ በሚያከናውኑ ነጋዴዎች ላይ  ተከታታይ ኦፕሬሽኖች ሲያከናውን ቆይቷል።

በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በተካሄዱ ኦፕሬሽኖች በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 294 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።

ኦፕሬሽኖቹ በመኪና መለዋወጫ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግንባታ ግብዓቶች፣ በሥጋ ቤቶች፣ በአልባሳት እንዲሁም በወለል ምንጣፍ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ መካሄዳ ቸውን አመልክቷል፡፡

በዚህም ከተጠርጣሪዎች መካከል 55ቱ ጉዳያቸው ለፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን፥ ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ከስድስት ወራት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ግለሰቦቹ የመንግሥትን ጥቅም ለማሳጣት ከታክስ አስተዳደር ዓዋጅ በተፃረረ መልኩ ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈፀም ወንጀል  መፈጸማቸው ተገልጿል።

የተቀሩት 239 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ በቀጣይም ያለደረሰኝ ግብይትና የግብር ስወራን ለመከላከል የሚከናወነው ተግባር እንደሚያጠናክር አስታውቋል።
ሕግና ፍትሕወንጀልቅጣት

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!