እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:46 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:46 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ስፖርት
ጎልፍ በአዲስ ምዕራፍ-በመከላከያ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
በአምስት ምድቦች ተከፋፍለው ወደ ሜዳ የገቡት 16 ምርጥ ሴት ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የተውጣጡ ናቸው።
1 / 2
በኢትዮጵያ የጎልፍ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አዲስ የታሪክ ገጽ ተገልጧል።
የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የሴቶች የጎልፍ ውድድር አረንጓዴው ሜዳ ላይ ለየት ያለ ውድድር አዘጋጅቷል።
ውድድሩ ስፖርታዊ ፉክክር ብቻ ሳይሆን፤ የሴቶችን ጥንካሬ፣ ሥልጣኔና አዲስ ራዕይን ያሳየ መድረክም ነበር።
በአምስት ምድቦች ተከፋፍለው ወደ ሜዳ የገቡት 16 ምርጥ ሴት ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የአ
ገር ውስጥ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የተውጣጡ ናቸወ።
በዚህ ውድድር ደግሞ ብርቱ ፉክክር በማድረግ የጽናት ተምሳሌት ሆነው የታዩት የመከላከያ ቅርስና ሙዚየም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ጥሩዬ አሰፌ ይባላሉ።
ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ በውድድሩ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩ ሲሆን፣ ስፖርቱ ለጤና ብቻ ሳይሆን ለአገርም የገቢ ምንጭ መሆን የሚችል ዘርፍ ነው ብለዋል።
ስፖርቱ በሰዎች መካከል ያለውን ዝምድና የሚያጠናክር የዲፕሎማሲ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም አንስተዋል።
በኢትዮጵያ ብቸኛውና ደረጃውን የጠበቀ የጎልፍ መጫወቻ ሜዳ በአገር መከላከያ ተቋም ውስጥ መገኘቱ ደግሞ ተቋሙ ለስፖርቱ እድገትና ለጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ይህ የመጀመሪያው የሴቶች የጎልፍ ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ለስፖርቱ አፍቃሪ ያስተዋወቀችበት መድረክ እንደነበር የአገር መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ይገልጻል።
ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬና መሰል ጠንካራ ሴቶች ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ አዲስ መንገድ ቀዳጆች ሆነዋል።
የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎልፍ ክለብ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ያስታወሱት ጄኔራል መኮንኗ፣ተቋሙ ባመቻቸው በዚህ ዕድል በመጠቀም ሁሉም ስፖርቱን የሕይወቱ አካል እንዲያደርገው ጥሪ አስተላልፈዋል።
ስፖርት
መከላከያ ሠራዊት
ጎልፍ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!