እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:44:23 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

ጎግል ሦስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን በፍለጋ አገልግሎቱ አካተተ

1 ደቂቃ ንባብ
ጎግል ሦስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን በፍለጋ አገልግሎቱ አካተተ
ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞና ሶማሊኛን የፍለጋ ቋንቋዎች ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ መረጃ ፈልገው የመጠቀም ዕድላቸውን ያሰፋዋል፡፡

ጎግል  ኩባንያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence - AI) የተደገፈ የፍለጋ አገልግሎቱን ለማሻሻል 13 የአፍሪካ ቋንቋዎችን እንዲደግፍ ማስፋፋቱን አስታወቀ። 

 ቋንቋዎች መካከል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ ፣ሃውሳ፣ ኪንያርዋንዳ፣ ኪስዋሂሊና ሌሎች ቋንቋዎች ተካትተዋል።

ኩባንያው የወሰደው እርምጃ በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ መረጃ ለመፈለግና ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በቀላሉ ለመገናኘት ዕድል ይፈጥራል።

የጎግል አዲሱ ባህሪ የሆነው ኤ አይ ምልከታ (AI Overviews) ተጠቃሚዎች ሲፈልጉ በአጭር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ  የተፈጠረ ማጠቃለያ መረጃ ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞድ (AI Mode) ደግሞ በጽሁፍ፣ በድምፅ ወይም በምስል ተጠቅመው ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጉዳዮችን በጥልቀት ለመመርመር ያግዛል። 

ይህ ዕድገት የአፍሪካ ቋንቋዎች በዲጂታል መድረኮች ውስጥ ያላቸውን ተወካይነት ለማሳደግና ተጠቃሚዎች በራሳቸው ቋንቋ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ እንደሚያበረታታ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መረጃ ያሳያል።

አርተፊሻል ኢንተለጀንስ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!