እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:41:21 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዚዳንት ፑቲን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ

1 ደቂቃ ንባብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዚዳንት ፑቲን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ
መሪዎቹ ዛሬ ያካሄዱት ውይይትበፖለቲካ፣ በንግድና በኢኮኖሚ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር በሚጠናከርባቸው መንገዶች ያተኮረ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጋራ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መከሩ።

ከመሪዎቹ ጸህፈት ቤቶች የወጡት መረጃዎች እንዳመለከቱት፤ መሪዎቹ በስልከ ያደረጉት ውይይት የአገሮቻቸውን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

አገሮቹ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ በመሥራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

በዚህም ሩሲያ ኢትዮጵያን የኑክሊዬር መሣሪያዎች ባለቤት ለማድረግ የጀመረችው ጥረት አንደኛው ማሳያ ነው።

በዚህ ዓመት መግቢያ ወደ ሞስኮ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሞስኮ በዓለም አውቶሚክ ሳምንት ጉባዔ ከመሳተፍ ባለፈ፤የኒዩክሊዬር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።

መሪዎቹ ከጉባዔው በተጓዳኝ በኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ በጤናና የመከላከያ  የተመለከቱ ጉዳዮች ላይም መነጋገራቸውን መረጀዎች ያመለክታሉ።

መሪዎቹ ዛሬ ያካሄዱት ውይይትም በፖለቲካ፣ በንግድና በኢኮኖሚ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር በሚጠናከርባቸው መንገዶች እንዳተኮረም ተመላክቷል።

 ፕሬዘዳንት ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ኅዘን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደገለጹላቸው የጽህፈት ቤታቸው  መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያና ሩሲያ ረጅም ዘመናት ባስቆጠረው ግንኙነታቸው ከጋራ ጥቅሞቻቸው ባሻገር፤ለአፍሪካና በማደግ ላይ ለሚገኙ አገሮች ሕዝቦች መብቶችና ጥቅሞች በመሥራት ይታወቃሉ።

አገሮቹ የብሪክስ አባላትም ሆነው በመሥራት ላይ ናቸው።

የውጭ ግንኙነትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድኢትዮ-ሩሲያዲፕሎማሲ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!