እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:47:05 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

ፍሬሕይወት የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት ቢዝነስ መሪ ሆነው ተመረጡ

1 ደቂቃ ንባብ
ፍሬሕይወት የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት ቢዝነስ መሪ ሆነው ተመረጡ
መጽሔቱ ዕውቅናውን የሰጠው ዋና ሥራ አስፈጻሚዊ በቴሌኮምና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ላስመዘገቡት የላቀ ስኬትና ባበረከቱት አስተዋጽዖ ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የ2026 የአፍሪካ ሴት ቢዝነስ መሪዎች መካከል ሆነው ተመረጡ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የዓመቱ ምርጥ የቢዝነስ መሪ ሆነው ዕወቅና የተሰጣቸው መቀመጫውን ለንደን፤እንግሊዝ ያደረገው አፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት ነው።

መጽሔቱ ዕውቅናውን የሰጠው ዋና ሥራ አስፈጻሚዊ ባለፉት ዓመታት በቴሌኮምና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ላስመዘገቡት የላቀ ስኬትና ባበረከቱት አስተዋጽዖ መሆኑን ተቋማቸው ያሰራጨው መረጃ ያሳያል።

ለዋና ሥራ አስፈጻሚዋ  የተሰጣቸው ዕውቅና ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ የተሰጠ ዓለም አቀፍ እውቅና ጭምር መሆኑንም አመልክቷል። 

"በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በሳል የለውጥ አመራር ብቃት፣ ኩባንያችን ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ወደ ሁለገብ የዲጂታል ተጠቃሚነት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ሚና የሚጫወት ዋና ሞተርነት መሸጋገር ችሏል" ብሏል። 

ኩባንያው "ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂን በመቅረጽና ተግባር ላይ በማዋል፣ ተቋሙነዠን በተሳካ ሁኔታ መምራት ብቻ ሳይሆን"፤ ለአገሪቱ የዲጂታል መጻኢ ዕድል ፅኑ መሠረት በማስቀመጥ ላይ እንደሚገኙም አመልክቷል፡፡ 

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ቴሌኮም በአፍሪካ ተወዳዳሪና ብቃት ያለው ዘርፍ  ሆኖ የሚወጣበት አቅም የፈጠረ ተቋም መሆኑን ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

ኩባንያው በአገር ውስጥ የቴሌኮምና ዲጂታል ዘርፍን ተደራሽ በማድረግ ካስመዘገበው ውጤት ባሻገር፤በጎረቤትና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ሲገልጽ ነበር።

ኢትዮ ቴሌኮምሳይንስና ቴክኖሎጂታዋቂ ሰዎች

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!