እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:43:47 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

‹‹በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ"

1 ደቂቃ ንባብ
‹‹በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ"
መነሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በማድረግ በሚካሄደው ውድድር 16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶችና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ይሳተፋሉ።
1 / 3

"በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሐሳብ ሩጫ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሁነቱን አስመልክቶ ዛሬ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ሩጫው በከተማዋ መጋቢት 13 ቀን 2018 አምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚከናወን ተገልጧል፡፡

መነሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በማድረግ በሚካሄደው ውድድር  16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶችና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ይሳተፋሉ።

የቅድሚያ ለሴቶች ውድድር አምባሳደር አትሌት መሠረት ደፋር፤ ሴቶች በዓላማ ጠንክረው ከሠሩ ያሰቡበት ደረጃ መድረስ ይችላሉ፤ እናንተ ለሀገር ተስፋዎች ናችሁና በርቱ ብላለች ስትል መልዕክት እስተላለፋለች።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አሰግደው ኃይለ ጊዮርጊ በወሩ አጋማሸ የሚካሄደው ሩጫ  አብሮነታችንን የምናሳይበት እንዲሆን አብረን እንሠራለን በማለት ተናግረዋል፡፡

ሩጫው "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚካሄድ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚያዘጋጀው  በሀለቱም ጾታዎች የ10 ኪሎ ሜትር ሌሎች ውድድሮች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ያካሂዳል፡፡

በኢትዮጵያ የታላቁ ሩጫ ውድድሮች ዘንድሮ 25 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡

 

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያየቅድሚያ ለሴቶች ውድድር

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!